Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “የሚ​ሳ​ደብ ይህ ማን ነው? ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ኀጢ​አ​ትን ማስ​ተ​ስ​ረይ ማን ይች​ላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም፣ “አምላክን በመሳደብ እንዲህ የሚናገር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጻፎችና ፈሪሳውያንም፦ “ስድብን የሚሰነዝር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ማን ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ይችላል?” እያሉ ያስቡ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማነው? ኃጢአትን የሚደመስስ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ ሌላ ማነው?” እያሉ ያስቡ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ጻፎችና ፈሪሳውያንም፦ ይህ የሚሳደብ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው ያስቡ ጀመር።

参见章节 复制




ሉቃስ 5:21
23 交叉引用  

እል​ፍ​ኙን በውኃ የሚ​ሠራ፥ ደመ​ናን መሄ​ጃው የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በነ​ፋስ ክን​ፍም የሚ​ሄድ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና ምጽ​ዋ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ምድ​ርን ሞላ።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ነው፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ትደ​ር​ሳ​ለች።


“ኑና እን​ዋ​ቀስ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነ​ጻ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠ​ራ​ዋ​ለሁ።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


መተ​ላ​ለ​ፍ​ህን እንደ ደመና፥ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም እንደ ጭጋግ ደም​ስ​ሼ​አ​ለሁ፤ ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና ወደ እኔ ተመ​ለስ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠርቶ የሚ​ሰ​ድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት፤ መጻ​ተኛ ወይም የሀ​ገር ልጅ ቢሆን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠርቶ ቢሳ​ደብ ይገ​ደል።


ተመልሶ ይምረናል፥ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።


በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።


እነሆም ከጻፎቹ አንዳንዶቹ በልባቸው “ይህስ ይሳደባል፤” አሉ።


እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ከዚ​ህም በኋላ፥ ከዕ​ለ​ታት በአ​ንድ ቀን ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው እን​ዲህ ሆነ፤ ከገ​ሊ​ላና ከይ​ሁዳ መን​ደ​ሮች፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የመጡ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የኦ​ሪት መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እር​ሱም ይፈ​ውስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነበረ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በል​ባ​ችሁ ምን ታስ​ባ​ላ​ችሁ?


በማ​ዕዱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ኀጢ​አ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ይህ ማነው?” ይሉ ጀመር።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ፥ ሰው ስት​ሆን ራስ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህና፤ ስለ መሳ​ደ​ብህ ነው እንጂ ስለ መል​ካም ሥራ​ህስ አን​ወ​ግ​ር​ህም” አሉት።


እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ካጸ​ደቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሰዎች የሚ​ቃ​ወ​ማ​ቸው ማነው?


跟着我们:

广告


广告