Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 መጽ​ሐ​ፉ​ንም አጥፎ ለተ​ላ​ላ​ኪው ሰጠ​ውና ተቀ​መጠ፤ በም​ኲ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ዐይ​ና​ቸ​ውን አት​ኲ​ረው ተመ​ለ​ከ​ቱት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም መጽሐፉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብ የነበሩትም ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጥቅል ብራናውንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ከሰጠ በኋላ ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሱስ መጽሐፉን አጥፎ ለአስተናባሪው ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኲራቡ የነበሩትም ሁሉ ትኲር ብለው ወደ እርሱ ይመለከቱ ጀመር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።

参见章节 复制




ሉቃስ 4:20
13 交叉引用  

በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፤ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።


ነገር ግን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ትም​ህ​ር​ቱን በመ​ስ​ማት ይመ​ሰጡ ነበ​ርና።


የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስ​ንም መጽ​ሐፍ ሰጡት፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም በገ​ለጠ ጊዜ እን​ዲህ የሚል የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ስፍራ አገኘ።


እር​ሱም፥ “የዚህ የመ​ጽ​ሐፍ ነገር ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ ደረሰ፤ ተፈ​ጸ​መም” ይላ​ቸው ጀመር።


ከሁ​ለቱ ታን​ኳ​ዎች ወደ አን​ዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺ​ውም ታንኳ የስ​ም​ዖን ነበ​ረች፤ “ከም​ድር ጥቂት እልፍ አድ​ር​ጋት” አለው፤ በታ​ን​ኳ​ዪ​ቱም ውስጥ ተቀ​ምጦ ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


በሰ​ን​በት ቀንም ከከ​ተ​ማዉ በር ወደ ባሕሩ ዳር ወጣን፤ በዚያ የጸ​ሎት ቤት ያለ መስ​ሎን ነበ​ርና፤ በዚ​ያም ተቀ​ም​ጠን፥ በዚያ ለተ​ሰ​በ​ሰቡ ሴቶች እና​ስ​ተ​ምር ጀመ​ርን።


ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?


跟着我们:

广告


广告