Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 22:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ተቈ​ጠረ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው በእኔ ይደ​ር​ሳል፤ ስለ እኔ የተ​ጻ​ፈ​ውም ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እላችኋለሁና፤ ‘ከዐመፀኞች ጋራ ተቈጠረ’ ተብሎ የተጻፈው በእኔ መፈጸም አለበት፤ ስለ እኔ የተጻፈው ፍጻሜው በርግጥ ደርሷል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ይህ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቈጠረ፤’ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ የግድ መፈጸም አለበት እላችኋልለሁ፤ አዎን፤ ስለ እኔ የተባለው አሁን ይፈጸማልና፤” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ስለ እኔ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ስለሚገባው ‘ከዐመፀኞች ጋር ተቈጠረ’ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በእኔ ላይ መፈጸም አለበት እላችኋለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እላችኋለሁና፥ ይህ፦ ከዓመፀኞች ጋር ተቈጠረ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ሊፈጸም ግድ ነው፤ አዎን፥ ስለ እኔ የሚሆነው አሁን ይፈጸማልና አላቸው።

参见章节 复制




ሉቃስ 22:37
17 交叉引用  

ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዴዎች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።


መጽሐፍም “ከዐመፀኞች ጋር ተቆጠረ፤” ያለው ተፈጸመ።


ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ወ​ጣ​ለን፤ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈው ሁሉ በሰው ልጅ ላይ ይፈ​ጸ​ማል።


የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በእጁ ለሚ​ሰ​ጥ​በት ለዚያ ሰው ወዮ​ለት።”


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮ​ጆ​ውን ይያዝ፤ ከረ​ጢ​ትም ያለው እን​ዲሁ ያድ​ርግ፤ ሰይፍ የሌ​ለ​ውም ልብ​ሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊይ​ዙት ወደ እርሱ የመ​ጡ​ትን የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችን፥ የቤተ መቅ​ደስ ሹሞ​ች​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሌባን እን​ደ​ም​ት​ይዙ በሰ​ይ​ፍና በጎ​መድ ልት​ይ​ዙኝ መጣ​ች​ሁን?


ሌሎች ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሊሰ​ቅሉ ወሰዱ።


እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የመ​ጣ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን አማ​ል​ክት ካላ​ቸው፥ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይታ​በል ዘንድ አይ​ቻ​ልም።


እኔ ልሠ​ራው የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ሥራ ፈጽሜ በም​ድር ላይ አከ​በ​ር​ሁህ።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


እኛ​ንስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እኛ የኦ​ሪ​ትን መር​ገም በመ​ሸ​ከሙ ከኦ​ሪት መር​ገም ዋጅ​ቶ​ናል፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በእ​ን​ጨት ላይ የተ​ሰ​ቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”


跟着我们:

广告


广告