Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 22:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ደግ​ሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረ​ጢ​ትና ያለ ጫማ በላ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ በውኑ የተ​ቸ​ገ​ራ​ች​ሁት ነገር ነበ​ርን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከዚያም ኢየሱስ፣ “ያለ ኰረጆ፣ ያለ ከረጢትና ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ምንም አልጐደለብንም” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ከዚያም፥ “ያለ ቦርሳና ያለ ከረጢት፥ ያለ ጫማም በላክኋችሁ ጊዜ፥ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “የገንዘብ ቦርሳ፥ ከረጢት፥ ጫማም ሳትይዙ በላክኋችሁ ጊዜ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም የጐደለብን ነገር አልነበረም” ሲሉ መለሱለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ደግሞም፦ ያለ ኮረጆና ያለ ከረጢት ያለ ጫማም በላክኋችሁ ጊዜ፥ አንዳች ጐደለባችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ አንዳች እንኳ አሉ።

参见章节 复制




ሉቃስ 22:35
16 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባ​ቶች አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ በፊቱ ደስ ያሰ​ኙት እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመ​ገ​በኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥


ፈር​ዖ​ንም፥ “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ ሀገ​ርህ መሄድ የፈ​ለ​ግህ ምን አጥ​ተህ ነው?” አለው። አዴ​ርም፥ “አን​ዳች አላ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ልሂድ” ብሎ መለሰ። አዴ​ርም ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ።


ምድር በሞ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናት፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


ከረ​ጢ​ትም፥ ስል​ቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አት​ያዙ፤ በመ​ን​ገ​ድም ማን​ንም ሰላም አት​በሉ።


እርሱ ግን፥ “ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ እን​ደ​ማ​ታ​ው​ቀኝ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” አለው።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮ​ጆ​ውን ይያዝ፤ ከረ​ጢ​ትም ያለው እን​ዲሁ ያድ​ርግ፤ ሰይፍ የሌ​ለ​ውም ልብ​ሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በት​ርም ቢሆን፥ ከረ​ጢ​ትም ቢሆን፥ እን​ጀ​ራም ቢሆን፥ ወር​ቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብ​ስም ቢሆን ለመ​ን​ገድ ምንም አት​ያዙ።


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ብዙ ያለው አላ​ተ​ረ​ፈም፤ ጥቂት ያለ​ውም አላ​ጐ​ደ​ለም።”


በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን መል​ካም ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ ሊፈ​ት​ንህ፥ ሊያ​ዋ​ር​ድ​ህም አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቁ​ትን መና በም​ድረ በዳ የመ​ገ​በ​ህን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ፥


跟着我们:

广告


广告