Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ መቼ ይደ​ረ​ጋል? ይህስ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜው፥ ምል​ክ​ቱስ ምን​ድን ነው?” ብለው ጠየ​ቁት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? ደግሞም ይህ እንደሚሆን ምልክቱ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነርሱም “መምህር ሆይ! እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሊሆን መቃረቡን የሚያሳየው ምልክቱ ምንድነው?” ብለው ጠየቁት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱም “መምህር ሆይ! ይህ የሚሆነው መቼ ነው? ይህስ የሚሆንበት ጊዜ መቃረቡን የምናውቅበት ምልክት ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት።

参见章节 复制




ሉቃስ 21:7
13 交叉引用  

እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” አሉት።


“ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤


እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይህ ሁሉ እስ​ኪ​ደ​ረግ ድረስ ይህቺ ትው​ልድ አታ​ል​ፍም።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ታያ​ላ​ች​ሁን? በእ​ዚህ ቦታ ድን​ጋይ በድ​ን​ጋይ ላይ የማ​ይ​ተ​ው​በ​ትና ሳይ​ፈ​ርስ የማ​ይ​ቀ​ር​በት ዘመን ይመ​ጣል።”


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብዙ​ዎች እኔ ክር​ስ​ቶስ ነኝ፤ ጊዜ​ውም ደር​ሶ​አል እያሉ በስሜ ይመ​ጣ​ሉና እን​ዳ​ያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ት​ላ​ችሁ አት​ሂዱ።


跟着我们:

广告


广告