Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 20:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ሙታን እን​ደ​ሚ​ነ​ሡስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ‘እኔ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ’ ብሎ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ዘንድ እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው ሙሴ ተና​ግ​ሮ​አል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ሙሴ ስለ ቍጥቋጦ በተጻፈው ታሪክ ውስጥ ጌታን፣ ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ’ በማለቱ ሙታን እንደሚነሡ ያሳያል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ሙታን እንደሚነሡ ግን ሙሴ እራሱ በቁጥቋጦው ታሪክ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ’ በማለቱ አስታወቀ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ስለ ሙታን ትንሣኤ ግን፥ ሙሴ ስለ ቊጥቋጦው እሳት በተናገረው ታሪክ ውስጥ፥ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ’ ብሎ ጠርቶታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ሙታን እንዲነሡ ግን ሙሴ ደግሞ በቍጥቋጦው ዘንድ ጌታን የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ በማለቱ አስታወቀ፤

参见章节 复制




ሉቃስ 20:37
10 交叉引用  

ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ ቆሞ​በት ነበር፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ አት​ፍራ፥ ይህ​ችን አንተ የተ​ኛ​ህ​ባ​ትን ምድር ለአ​ን​ተም ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለሁ፤


ወደ አባ​ቴም ቤት በጤና ቢመ​ል​ሰኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ይሆ​ን​ል​ኛል፤


ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ሆይ፥ የአ​ባቴ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድ​ርህ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​በ​ትም ስፍራ ተመ​ለስ፤ በጎ​ነ​ት​ንም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ’ ያል​ኸኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥


ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን አለው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ትላ​ለህ፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እና​ንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረ​ስም መታ​ሰ​ቢ​ያዬ ይህ ነው።


በየ​ወ​ቅ​ቱም ከም​ድ​ሪቱ ምላት፥ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ ከነ​በ​ረው በረ​ከት፥ በዮ​ሴፍ ራስ ላይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም በከ​በ​ረው በእ​ርሱ ራስ ላይ ይው​ረድ።


跟着我们:

广告


广告