Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 2:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ከአ​ሴር ወገን የም​ት​ሆን የፋ​ኑ​ኤል ልጅ ሐና የም​ት​ባል ነቢ​ይት ነበ​ረች፤ አር​ጅ​ታም ነበር፤ ከድ​ን​ግ​ል​ና​ዋም በኋላ ከባል ጋር ሰባት ዓመት ኖረች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ደግሞም ከአሴር ወገን የሆነች የፋኑኤል ልጅ፣ ሐና የምትባል ነቢይት በዚያ ነበረች፤ እርሷም በጣም አርጅታ ነበር፤ በድንግልናዋ ካገባችው ባሏም ጋራ ሰባት ዓመት የኖረች ነበረች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ከአሴር ወገንም የሆነች የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ በዕድሜዋም በጣም የገፋች ነበረች፤ እርሷም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እንዲሁም በዚያን ጊዜ ከአሴር ነገድ የሆነች የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች። በዕድሜዋም በጣም የገፋች ሴት ነበረች፤ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ከተቀመጠች በኋላ ባልዋ ሞተባት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ እርስዋም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች፤

参见章节 复制




ሉቃስ 2:36
18 交叉引用  

ልያም፥ “እኔ ብፅ​ዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛ​ልና” አለች፤ ስሙ​ንም አሴር ብላ ጠራ​ችው።


እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኬል​ቅ​ያ​ስና አኪ​ቃም ዓክ​ቦ​ርም ሳፋ​ንና ዓሳ​ያም ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢ​ዪቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በዚያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ነገ​ሩ​አት።


በወ​ራቱ የደ​ረሰ አዝ​መራ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ፥ የእ​ህሉ ነዶም በወ​ቅቱ ወደ አው​ድማ እን​ዲ​ገባ፥ በረ​ዥም ዕድሜ ወደ መቃ​ብር ትገ​ባ​ለህ።


የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።


“አን​ተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! ከል​ባ​ቸው አን​ቅ​ተው ትን​ቢት በሚ​ና​ገሩ በሕ​ዝ​ብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊት​ህን አድ​ርግ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​ባ​ቸው፤


ባንቺ ግን በል​ብሽ ፍላጻ ይገ​ባል፤ የብ​ዙ​ዎ​ቹን ዐሳብ ይገ​ልጥ ዘንድ።”


ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ድኅ​ነት ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተና​ገ​ረች።


በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ባሮች ላይም ያን​ጊዜ መን​ፈ​ሴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ትን​ቢ​ትም ይና​ገ​ራሉ።


ለእ​ር​ሱም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ አራት ደና​ግል ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት።


ራስ​ዋን ሳት​ከ​ና​ነብ የም​ት​ጸ​ልይ ወይም የም​ታ​ስ​ተ​ምር ሴት ሁላ ራስ​ዋን ታዋ​ር​ዳ​ለች፤ ራስ​ዋን እንደ ተላ​ጨች መሆ​ንዋ ነውና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ስጦ​ታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አላ​ዋ​ቆች ልት​ሆኑ አን​ወ​ድ​ድም።


እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥


ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፤ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤


አም​ስ​ተ​ኛው ዕጣ ለአ​ሴር ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ።


ከአሴር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከምናሴ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


በዚ​ያም ወራት ነቢ​ይቱ የለ​ፊ​ዶት ሚስት ዲቦራ እስ​ራ​ኤ​ልን ትገ​ዛ​ቸው ነበ​ረች።


ሁለ​ትም ሚስ​ቶች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ሐና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍ​ና​ናም ልጆች ነበ​ሩ​አት፤ ለሐና ግን ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


跟着我们:

广告


广告