Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ድን​ገ​ትም ከዚያ መል​አክ ጋር ብዙ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገኑ መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ድንገትም ብዙ የሰማይ ሰራዊት ከመልአኩ ጋራ ታዩ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ እንዲህ አሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በድንገት ብዙ የሰማይ መላእክት ከመልአኩ ጋር አብረው ታዩ፤ እግዚአብሔርንም በማመስገን፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦

参见章节 复制




ሉቃስ 2:13
18 交叉引用  

ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር።


ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።


ከዋ​ክ​ብት በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ መላ​እ​ክቴ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ አመ​ሰ​ገ​ኑኝ


መላ​እ​ክቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤ ሠራ​ዊቱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።


መን​ፈ​ስም ወደ ላይ ወሰ​ደኝ፤ በኋ​ላ​ዬም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ከቦ​ታው ይባ​ረክ” የሚል የታ​ላቅ ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ እን​ዲሁ ንስሓ ስለ​ሚ​ገባ ስለ አንድ ኀጢ​ኣ​ተኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ፊት በሰ​ማ​ያት ደስታ ይሆ​ናል።”


ለእ​ና​ን​ተም ምል​ክቱ እን​ዲህ ነው፦ ሕፃን አውራ ጣቱን ታስሮ፥ በጨ​ር​ቅም ተጠ​ቅ​ልሎ በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ ታገ​ኛ​ላ​ቸሁ።”


“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።


ብዙ ልዩ ልዩ የሆ​ነች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኩል በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለ​ቆ​ችና ሥል​ጣ​ናት ትታ​ወቅ ዘንድ፤


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤


跟着我们:

广告


广告