Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 16:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ሐምራዊና ቀጭን በፍታ የለበሰ፣ በየቀኑም በተድላ ደስታ የሚኖር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “በሐምራዊና በክት ልብስ የሚሽቀረቀር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በቅንጦት ይኖር ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ቀይ ከፋይና ቀጭን ልብስ የሚለብስ አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ እርሱም በየቀኑ በቅንጦት ይኖር ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር።

参见章节 复制




ሉቃስ 16:19
23 交叉引用  

ዐዋቂ ሰው የጠቢባን ዘውድ ነው፤ የአላዋቂዎች ተግባር ግን ክፉ ነው።


መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።


በወ​ር​ቅና በብር አጌ​ጥሽ፤ ልብ​ስ​ሽም ጥሩ በፍ​ታና ሐር፥ ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አን​ቺም መል​ካ​ምን ዱቄ​ትና ማርን፥ ዘይ​ት​ንም በላሽ፤ ወፈ​ርሽ፤ እጅ​ግም ውብ ሆንሽ፤ ለመ​ን​ግ​ሥ​ትም የተ​ዘ​ጋ​ጀሽ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።


እነሆ የእ​ኅ​ትሽ የሰ​ዶም ኀጢ​አት ይህ ነበረ፤ ትዕ​ቢት፥ እን​ጀ​ራን መጥ​ገብ፥ መዝ​ለ​ልና ሥራን መፍ​ታት፥ ይህ ሁሉ በእ​ር​ስ​ዋና በል​ጆ​ችዋ ነበር፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንና የድ​ሀ​ው​ንም እጅ አላ​ጸ​ና​ችም።


ዓላማ እን​ዲ​ሆ​ን​ልሽ ሸራሽ ከግ​ብፅ በፍ​ታና ከወ​ርቀ ዘቦ ተሠ​ር​ቶ​አል፤ መደ​ረ​ቢ​ያ​ሽም ከኤ​ሊሳ ደሴ​ቶች ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ሐር ተሠ​ር​ቶ​አል።


ቀይ ልብስም አለበሱት፤ የእሾህ አክሊልም ጐንጕነው ደፉበት፤


ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መጋቢ የነ​በ​ረው አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ እን​ደ​ሚ​በ​ትን አድ​ር​ገው በእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ሱት።


“ሚስ​ቱን ፈትቶ ሌላ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገባ ሁሉ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ ባልዋ የፈ​ታ​ት​ንም የሚ​ያ​ገባ ያመ​ነ​ዝ​ራል።


በቍ​ስል ሕመም ተይዞ በባ​ለ​ጸ​ጋው ደጅ የወ​ደቀ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል አንድ ድሃም ነበረ።


ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤


“በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤


ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥


የለ​መ​ነ​ውም የወ​ርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአ​ም​ባሩ፥ ከድ​ሪ​ውም፥ የም​ድ​ያ​ምም ነገ​ሥ​ታት ከለ​በ​ሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት ከነ​በ​ሩት ሥሉ​ሴ​ዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告