Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 12:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ያላችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ፤ ሌባ በማይሰርቅበት፣ ብል በማይበላበት፣ በማያረጅ ከረጢት የማያልቅ ሀብት በሰማይ አከማቹ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ያላችሁን ሽጡ፤ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ያላችሁን ሁሉ ሸጣችሁ ገንዘቡን ለድኾች ስጡ፤ የማያረጅ የገንዘብ ቦርሳም አዘጋጅታችሁ ገንዘባችሁን ሌባ በማይደርስበት፥ ብል በማይበላበትና ከቶም በማያልቅበት ቦታ በመንግሥተ ሰማያት አስቀምጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤

参见章节 复制




ሉቃስ 12:33
14 交叉引用  

ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥ ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።


ኢየሱስም “ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው።


ነገር ግን የሚ​ወ​ደ​ደ​ውን ምጽ​ዋት አድ​ር​ጋ​ችሁ ስጡ፤ ሁሉም ንጹሕ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።


ሀብ​ትን ለራሱ የሚ​ሰ​በ​ስብ፤ ሀብ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ሆነ እን​ዲሁ ነው።”


እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ባለ​ቀ​ባ​ችሁ ጊዜ እነ​ርሱ በዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ይቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ዘንድ በዐ​መፃ ገን​ዘብ ለእ​ና​ንተ ወዳ​ጆች አድ​ር​ጉ​በት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።”


ይህ​ንም ያለ፥ ድሆች አሳ​ዝ​ነ​ውት አይ​ደ​ለም፤ ሌባ ነበ​ርና፥ ሙዳየ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ሲጠ​ብቅ በው​ስጡ ከሚ​ገ​ባው ይወ​ስድ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ነው እንጂ።


መሬ​ታ​ቸ​ው​ንና ጥሪ​ታ​ቸ​ው​ንም እየ​ሸጡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ደ​ሚ​ያ​ሻው ይሰጡ ነበር።


በብዙ መከራ ከመ​ፈ​ተ​ና​ቸው የተ​ነሣ ደስ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፤ በድ​ህ​ነ​ታ​ቸው ጥል​ቅ​ነ​ትም የለ​ጋ​ስ​ነ​ታ​ቸው ባለ​ጠ​ግ​ነት በዝ​ታ​ለ​ችና።


跟着我们:

广告


广告