Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 11:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ይህን ሲነ​ግ​ራ​ቸው ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን አጽ​ን​ተው ይጣ​ሉት፥ ይቀ​የ​ሙ​ትም ጀመር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 ኢየሱስ ከዚያ ከወጣ በኋላ፣ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ክፉኛ ይቃወሙትና በጥያቄም ያዋክቡት ጀመር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 እርሱም ከዚያ ወጥቶ በመሄድ ላይ ሳለ ጻፎችና ፈሪሳውያን እርሱን እጅግ በመቃወም ስለ ብዙ ነገሮች የትንኮሳን ጥያቄ ይጠይቁት ጀመር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ሊሄድ በተነሣ ጊዜ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ይቃወሙትና ብዙ ጥያቄም ያቀርቡለት ጀመር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53-54 ይህንም ሲናገራቸው፥ ጻፎችና ፈሪሳውያን በአፉ የተናገረውን ሊነጥቁ ሲያደቡ፥ እጅግ ይቃወሙና ስለ ብዙ ነገር እንዲናገር ያነሣሡ ጀመር።

参见章节 复制




ሉቃስ 11:53
11 交叉引用  

ጠላ​ቶ​ቹን ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ሥ​ራቅ፥ አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ዕ​ራብ ያን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​በ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ከ​ፈተ አፍ ይበ​ሉ​ታል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ።


እና​ንተ ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! የጽ​ድ​ቅ​ንና የዕ​ው​ቀ​ትን መክ​ፈቻ ወስ​ዳ​ችሁ ትሰ​ው​ራ​ላ​ች​ሁና፤ እና​ን​ተም አት​ገ​ቡ​ምና፤ የሚ​ገ​ቡ​ት​ንም መግ​ባ​ትን ትከ​ለ​ክ​ሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”


በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ሊያ​ስ​ቱ​ትና ሊያ​ጣ​ሉት ያደ​ቡ​በት ነበር።


ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይ​ተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚ​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትን አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ያስ​ቱት ዘንድ ወደ መኳ​ን​ን​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት አሳ​ል​ፈው ሊሰ​ጡት ራሳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ጻ​ድቁ ሰላ​ዮ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።


“ሙታን አይ​ነ​ሡም” ከሚሉ ከሰ​ዱ​ቃ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ።


“እኔም ብዙ ጊዜ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ስም ላይ ክፉ ነገር ላደ​ርግ ቈርጬ ነበር።


ብቻ​ዬን ይድ​ላኝ አያ​ሰ​ኝም፤ አያ​በ​ሳ​ጭም፤ ክፉ ነገ​ር​ንም አያ​ሳ​ስ​ብም።


ይህ​ንም የቸ​ር​ነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ ዘንድ ቲቶን ማለ​ድ​ነው።


跟着我们:

广告


广告