Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ በአ​ን​ዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎ​ቱን በጨ​ረሰ ጊዜም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐ​ንስ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንደ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ጸሎት አስ​ተ​ም​ረን” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም እንደ ጨረሰ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “ጌታ ሆይ፤ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው አንተም መጸለይን አስተምረን” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንዲሁ መጸለይን አስተምረን፤” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም ባበቃ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው፥ አንተም እኛን መጸለይ አስተምረን!” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።

参见章节 复制




ሉቃስ 11:1
14 交叉引用  

ጥቂት ይበ​ቃል፤ ያም ባይ​ሆን አንድ ይበ​ቃል፤ ማር​ያ​ምስ የማ​ይ​ቀ​ሙ​አ​ትን መል​ካም ዕድል መረ​ጠች።”


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በም​ት​ጸ​ል​ዩ​በት ጊዜ እን​ዲህ በሉ፦ በሰ​ማ​ያት የም​ት​ኖር አባ​ታ​ችን ሆይ፥ ስምህ ይቀ​ደስ፤ መን​ግ​ሥ​ትህ ትምጣ፤ ፈቃ​ድህ በሰ​ማይ እንደ ሆነ እን​ዲ​ሁም በም​ድር ይሁን።


በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤


ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት።


ዮሐ​ን​ስም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ላካ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ብቻ​ውን ሲጸ​ልይ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ሳሉ፥ “ሰዎች ማን ይሉ​ኛል?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ጴጥ​ሮ​ስን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዮሐ​ን​ስን ይዞ​አ​ቸው ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ።


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥


跟着我们:

广告


广告