Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 1:66 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

66 የሰ​ሙ​ትም ሁሉ፥ “እን​ግ​ዲህ ይህ ሕፃን ምን ይሆን?” እያሉ በል​ባ​ቸው አኖ​ሩት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

66 ይህንም የሰሙ ሁሉ፣ “ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ያዙ፤ የጌታ እጅ በርግጥ ከርሱ ጋራ ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

66 የሰሙትም ሁሉ፥ “እንግዲህ ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ በልባቸው አኖሩት፤ በእርግጥ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

66 ይህን ነገር የሰሙ ሁሉ፥ “ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ይጠያየቁ ነበር። ይህም የሆነው የእግዚአብሔር ረድኤት በእርግጥ ከእርሱ ጋር ስለ ነበር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

66 የሰሙትም ሁሉ፦ እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት፤ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና።

参见章节 复制




ሉቃስ 1:66
16 交叉引用  

ወን​ድ​ሞ​ቹም ቀኑ​በት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠ​ብ​ቀው ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በኤ​ል​ያስ ላይ ነበ​ረች፤ ወገ​ቡ​ንም ታጥቆ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል እስ​ኪ​ገባ ድረስ በአ​ክ​ዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።


ማር​ያም ግን ይህን ሁሉ ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር።


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝ​ሬት ወረደ፤ ይታ​ዘ​ዝ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር።


“እና​ን​ተስ ይህን ነገር በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት፤ የሰው ልጅ በሰ​ዎች እጅ ተላ​ልፎ ይሰጥ ዘንድ አለ​ውና።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ወደ ጌታም ተመ​ል​ሰው ያመኑ ሰዎች ቍጥ​ራ​ቸው በዛ።


የእ​ው​ነት ቃል በሆ​ነው በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት፥ አስ​ቀ​ድሞ ስለ ሰማ​ች​ሁት፥ በሰ​ማይ ስለ ተዘ​ጋ​ጀ​ላ​ችሁ ተስ​ፋ​ች​ሁም እን​ጸ​ል​ያ​ለን።


ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ።


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።


跟着我们:

广告


广告