Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 1:64 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

64 ያን​ጊ​ዜም አፉ ተከ​ፈተ፤ አን​ደ​በ​ቱም ተና​ገረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

64 ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱ ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ መናገር ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

64 ያንጊዜም አፉ ተከፈተ፤ ምላሱም ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ተናገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

64 በዚያኑ ጊዜ ዘካርያስ አንደበቱ ተፈቶለት መናገር ቻለ፤ እግዚአብሔርንም ማመስገን ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

64 ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።

参见章节 复制




ሉቃስ 1:64
14 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደን​ቆ​ሮስ፥ የሚ​ያ​ይስ፥ ዕው​ርስ የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጁን ዘር​ግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “እነሆ፥ ቃሌን በአ​ፍህ ውስጥ አኑ​ሬ​አ​ለሁ፤


“በዚያ ቀን ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ቀን​ድን አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለአ​ንተ የተ​ከ​ፈተ አፍን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ነገር ግን በተ​ና​ገ​ር​ሁህ ጊዜ አፍ​ህን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ሰማ ይስማ፤ እንቢ የሚ​ልም እንቢ ይበል” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ያመ​ለ​ጠ​ውም ሳይ​መጣ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ በነ​ጋ​ውም ወደ እኔ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከ​ፈ​ተች፤ ከዚ​ያም በኋላ እኔ ዲዳ አል​ሆ​ን​ሁም።


ጋኔኑንም ካወጣው በኋላ ድዳው ተናገረ። ሕዝቡም “እንዲህ ያለ በእስራኤል ዘንድ ከቶ አልታየም፤” እያሉ ተደነቁ።


አሁ​ንም በጊ​ዜው የሚ​ሆ​ነ​ው​ንና የሚ​ፈ​ጸ​መ​ውን ነገ​ሬን አላ​መ​ን​ኽ​ኝ​ምና ይህ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ መና​ገ​ርም ይሳ​ን​ሃል።”


跟着我们:

广告


广告