Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 8:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አዝ​ዞ​ኛ​ልና እን​ዳ​ት​ሞቱ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሌሊ​ቱ​ንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀ​መጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐት ጠብቁ፤”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እንዳትሞቱ ሰባቱን ቀንና ሌሊት ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለዩ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐት ጠብቁ፤ የታዘዝሁት እንዲህ ነውና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እንዳትሞቱም የጌታን ትእዛዝ እየጠበቃችሁ፥ ለሰባት ቀን ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቀመጣላችሁ፤ እኔ እንዲህ ታዝዣለሁና።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ስለዚህም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ በመፈጸም ሰባት ቀን ሙሉ ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቈያላችሁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ ይህ እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሕግ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እግዚአብሔር እንዲሁ አዝዞኛልና እንዳትሞቱ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሌሊቱንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀመጡ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓት ጠብቁ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 8:35
24 交叉引用  

እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዛ​ቱን፥ ፍር​ዱ​ንና ምስ​ክ​ሩ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ።


“እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ሁሉ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ እን​ዲህ አድ​ርግ፤ ሰባት ቀን እጆ​ቻ​ቸ​ውን ትቀ​ድ​ሳ​ለህ።


ሰባት ቀንም በየ​ዕ​ለቱ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ከበ​ጎ​ችም አንድ ጠቦት በግ ያቀ​ር​ባሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋ​ው​ያን እንደ ሳቱ ላል​ሳ​ቱት፥ ሥር​ዐ​ቴን ለጠ​በ​ቁት፥ ከሳ​ዶቅ ልጆች ወገን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ካህ​ናት ይሆ​ናል።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ናዳ​ብና አብ​ዩድ በየ​ራ​ሳ​ቸው ጥና​ውን ወስ​ደው እሳት አደ​ረ​ጉ​በት፤ በላ​ዩም ዕጣን ጨመ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዛ​ቸ​ውን ሌላ እሳት አቀ​ረቡ።


የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


ሙሴም ከቅ​ብ​ዐቱ ዘይ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ከአ​ለው ከደሙ ወስዶ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ ፥ በል​ጆ​ቹና በል​ጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮ​ን​ንና ልብ​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብስ ቀደሰ።


በዚህ ቀን እንደ ተደ​ረገ ለእ​ና​ንተ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ይደ​ረግ ዘንድ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዘዘ።


አሮ​ንና ልጆ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ።


እን​ደ​ዚሁ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ያነ​ጻል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ ንጹሕ አይ​ሆ​ንም።


የድ​ን​ኳ​ኑን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሕጉ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ይጠ​ብቁ።


ደመ​ና​ውም በድ​ን​ኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተ​ቀ​መጠ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደድ፤ ሕጉ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም፥ ፍር​ዱ​ንም በዘ​መ​ንህ ሁሉ ጠብቅ።


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤


አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ ማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።


ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤


በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤


ኦሪ​ትስ የሚ​ሞት ሰውን ሊቀ ካህ​ናት አድ​ርጋ ትሾ​ማ​ለች፤ ከኦ​ሪት በኋላ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ሐላ ቃሉ ግን ዘለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ለ​ወጥ ፍጹም ወል​ድን ካህን አድ​ርጎ ሾመ​ልን።


跟着我们:

广告


广告