Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እርሱ ቢበ​ድ​ልና ከዚህ በኋላ ንስሓ ቢገባ፥ በቅ​ድ​ሚያ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወይም በዐ​መ​ፅና በግፍ የተ​ቀ​በ​ለ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​ጠ​ውን አደራ፥ ወይም ጠፍቶ ያገ​ኘ​ውን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚህ ሁኔታ ኀጢአት ቢሠራና በደለኛ ቢሆን፣ የሰረቀውን ወይም የቀማውን ወይም በዐደራ የተሰጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን ይመልሳል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እርሱም ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ቢሆን፥ በቅሚያ የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም በአደራ ከእርሱ ዘንድ የተቀመጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ማንም ሰው እነዚህን በደሎች ፈጽሞ ኃጢአተኛ ቢሆን፥ በቅሚያና በማታለል የወሰደውን፥ በዐደራ የተቀበለውንና ጠፍቶ ያገኘውን ንብረት ይመልስ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እርሱ ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ቢሆን፥ በቅሚያ የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም የተሰጠውን አደራ ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 6:4
20 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም አቤ​ሜ​ሌ​ክን ብላ​ቴ​ኖቹ በቀ​ሙት በውኃ ጕድ​ጓድ ምክ​ን​ያት ወቀ​ሰው።


እር​ሻ​ቸ​ውን፥ የወ​ይ​ና​ቸ​ው​ንና የወ​ይ​ራ​ቸ​ውን ቦታ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የወ​ሰ​ዳ​ች​ሁ​ትን ገን​ዘ​ቡ​ንና እህ​ሉን፥ ወይን ጠጁ​ንና ዘይ​ቱን እባ​ካ​ችሁ ዛሬ መል​ሱ​ላ​ቸው።”


የደ​ካ​ሞ​ችን ቤቶች አፍ​ር​ሶ​አ​ልና፤ ያል​ሠ​ራ​ው​ንም ቤት በዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።


ኃጥ​ኣን የድ​ን​በ​ሩን ምል​ክት አለፉ፤ እረ​ኛ​ው​ንም ከመ​ን​ጋ​ዎቹ ጋር ይነ​ጥ​ቃሉ።


የሸ​ረ​ሪ​ቶች ድር ልብስ አይ​ሆ​ንም፤ በሥ​ራ​ቸ​ውም ራሳ​ቸ​ውን አያ​ለ​ብ​ሱም፤ ሥራ​ቸው የግፍ ሥራ ነውና።


ድሀ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ቢያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ቢቀ​ማም፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​መ​ልስ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ጣዖ​ታት ቢያ​ነሣ፥ ርኩ​ስ​ንም ነገር ቢያ​ደ​ርግ፥


አባቱ ግን ፈጽሞ በድ​ሎ​አ​ልና፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ቀም​ቶ​አ​ልና፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ክፉን ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና እነሆ እርሱ በበ​ደሉ ይሞ​ታል።


ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያ​ዣ​ውን ቢመ​ልስ፥ ፈጽ​ሞም ባይ​ቀማ፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ከል​ብሱ ቢያ​ለ​ብስ፤


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም መያ​ዣን ቢመ​ልስ፥ የነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ቢከ​ፍል፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ትእ​ዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢ​አ​ትም ባይ​ሠራ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።


እን​ስ​ሳ​ንም ቢገ​ድል በነ​ፍስ ፋንታ ነፍስ ይክ​ፈል።


ሰው​ንም የመ​ታና የገ​ደለ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ወይ​ፈ​ኑን ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደ​ሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ አመድ በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።


“በፊቷ የሚ​መ​ጣ​ባ​ትን አላ​ወ​ቀ​ችም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሀ​ገ​ራ​ቸው ቅሚ​ያ​ንና ግፍን የሚ​ያ​ከ​ማቹ ናቸው።”


በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።


በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።


እናንተ፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፣ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፣ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።


ያች ሰው​ነት ብት​ና​ዘዝ፥ ያደ​ረ​ገ​ች​ው​ንም ኀጢ​አት ሁሉ ብት​ና​ገር የወ​ሰ​ደ​ውን ዓይ​ነ​ቱን ሁሉ ይመ​ልስ። አም​ስ​ተኛ እጅም ለባለ ገን​ዘቡ ይጨ​ምር።


跟着我们:

广告


广告