ዘሌዋውያን 6:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የኀጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኀጢአቱ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል፤ እርሱም ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘ስለ ኀጢአት መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኀጢአቱም መሥዋዕት እዚያው በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ፤ ይህም እጅግ ቅዱስ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአቱ መሥዋዕት በጌታ ፊት ይታረዳል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበው እንስሳ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ። ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአቱ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል፤ እርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። 参见章节 |