Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ያለ እርሾ መጋገር አለበት፤ በእሳት ከሚቀርብልኝ ቍርባን ይህን የእነርሱ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም፣ እንደ ኀጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በእርሾ ቦክቶ አይጋገርም። እርሱን በእሳት የሚቀርብ ቁርባኔ አድርጌ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጠሁ፤ እርሱም እንደ ኃጢአትና እንደ በደል መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እርሾ ተጨምሮበት አይጋገርም፤ ከሚነድ ቊርባኔ ለእነርሱ ድርሻ እንዲሆን የሰጠኋቸውና እንደ ኃጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በእርሾ ቦክቶ አይጋገርም። እርሱን ከእሳቱ ቍርባኔ ለእነርሱ እድል ፈንታ እንዲሆን ሰጠሁ፤ እርሱም እንደ ኃጢአትና እንደ በደል መሥዋዕት ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 6:17
14 交叉引用  

ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል።


ሙሴም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል እጅግ ፈለ​ገው፤ በፈ​ለ​ገ​ውም ጊዜ እነሆ ተቃ​ጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀ​ሩ​ትን የአ​ሮ​ንን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ተቈ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፦


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ እርሾ አይ​ሁ​ን​በት፤ እርሾ ያለ​በት ነገር፥ ማርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ አታ​ቀ​ር​ቡ​ምና።


ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም የተ​ረ​ፈው ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሆ​ናል፤ ይህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የተ​ረፈ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታ​ረ​ዳል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል።


ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእ​ርሱ ይበ​ላል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራም ይበ​ሉ​ታል፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት እንደ ሆነ እን​ዲሁ የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለሁ​ለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ካህን ይወ​ስ​ደ​ዋል።


“እርሱም ኀጢአት አላደረገም፤ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤”


跟着我们:

广告


广告