Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 27:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የረ​ከ​ሰም እን​ስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤ​ዠው፤ በእ​ር​ሱም የዋ​ጋ​ውን አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ባይ​ቤ​ዥም እንደ ግምቱ ይሸ​ጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እንስሳው ርኩስ ከሆነ ግን፣ ባለቤቱ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ ዐምስተኛ ጨምሮ ሊዋጀው ይችላል፤ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ ይሸጥ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምትህ መጠን ይቤዠዋል፤ በእርሱም ዋጋ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምትህ ይሸጣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ንጹሕ ያልሆነ የእንስሳ በኲር ግን በይፋ በታወቀው ዋጋ ላይ በመቶ ኻያ እጅ ተጨምሮበት እንደገና መዋጀት ይችላል፤ ባለቤቱ የማይዋጀው ከሆነ ግን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሌላ ሰው ይሸጥ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የረከሰም እንስሳ ቢሆን እንደ ግምቱ ይቤዠው፥ በእርሱም የዋጋውን አምስተኛ ይጨምርበታል፤ ባይቤዥም እንደ ግምቱ ይሸጣል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 27:27
7 交叉引用  

እን​ስ​ሳው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት መሆን የማ​ይ​ገ​ባው ርኩስ ቢሆን፥ እን​ስ​ሳ​ውን በካ​ህኑ ፊት ያቁ​መው።


ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ግን ከግ​ምቱ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር።


የተ​ሳ​ለ​ውም ሰው ቤቱን ይቤ​ዠው ዘንድ ቢወ​ድድ ከግ​ምቱ ገን​ዘብ በላይ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​ምር፤ ቤቱም ለእ​ርሱ ይሆ​ናል።


“ከእ​ን​ስ​ሳህ የሚ​ወ​ለድ በኵር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ማንም ይለ​ው​ጠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እን​ስሳ ወይም የር​ስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይ​ሸ​ጥም፤ አይ​ቤ​ዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ሰውም ዐሥ​ራ​ቱን ሊቤዥ ቢወ​ድድ፥ አም​ስ​ተኛ እጅ ይጨ​መ​ር​በ​ታል።


በተ​ቀ​ደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ዕዳ ይከ​ፍ​ላል፤ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል። ካህ​ኑም በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


跟着我们:

广告


广告