Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 25:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 በሥራ አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 በጭካኔ አትግዛቸው፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 በጽኑ እጅ አትግዛው፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 እነርሱን በማስጨነቅ አትግዛቸው፤ ነገር ግን እኔን አምላክህን ፍራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 በጽኑ እጅ አትግዛው፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 25:43
23 交叉引用  

በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


አሁ​ንም የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ልጆች ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገን እን​ግዛ ትላ​ላ​ችሁ፤ የፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር የም​ሆን እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር ያለሁ አይ​ደ​ለ​ምን?


“ወንድ ባሪ​ያዬ ወይም ሴት ባሪ​ያዬ በእኔ ዘንድ በተ​ም​ዋ​ገቱ ጊዜ፥ ፍር​ዳ​ቸ​ውን አዳ​ልቼ እንደ ሆነ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​መ​ረኝ ጊዜ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ? በጐ​በ​ኘኝ ጊዜስ በፊቱ ምን እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ?


አዋ​ላ​ጆች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈሩ፤ የግ​ብፅ ንጉ​ሥም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ወን​ዶ​ቹን ሕፃ​ና​ት​ንም አዳ​ኑ​አ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አዋ​ላ​ጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ​ፈሩ ቤቶ​ችን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


ከዚ​ያም ከብዙ ቀን በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከባ​ር​ነት የተ​ነሣ አለ​ቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባር​ነ​ታ​ቸ​ውም ጩኸ​ታ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ውን ግፍ ደግሞ አየሁ።


የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደ​ር​ጉት እንደ ነበ​ራ​ችሁ እንደ ትና​ን​ት​ና​ውና እንደ ትና​ን​ትና በስ​ቲ​ያው የተ​ቈ​ጠ​ረ​ውን ጡብ ዛሬስ ስለ​ምን አት​ጨ​ር​ሱም?” እያሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆች ይገ​ርፉ ነበር።


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


“ስለ ምን ጾምን፥ አን​ተም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ኸ​ንም? ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ስለ ምን አዋ​ረ​ድን፥ አን​ተም አላ​ወ​ቅ​ኸ​ንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾ​ማ​ችሁ ቀን ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፥ ሠራ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ታስ​ጨ​ን​ቃ​ላ​ችሁ።


የደ​ከ​መ​ውን አላ​ጸ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የታ​መ​መ​ው​ንም አል​ፈ​ወ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የተ​ሰ​በ​ረ​ው​ንም አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁ​ትም፤ የባ​ዘ​ነ​ው​ንም አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ትም፤ የጠ​ፋ​ው​ንም አል​ፈ​ለ​ጋ​ች​ሁ​ትም፤ በኀ​ይ​ልና በጭ​ቈ​ናም ገዛ​ች​ኋ​ቸው።


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አያ​ስ​ጨ​ንቅ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ።


ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ቸው ባሪ​ያ​ዎች ናቸ​ውና ባሪያ እን​ደ​ሚ​ሸጥ አይ​ሸጡ።


ምን ያህል ወንድ ባሪ​ያና ሴት ባሪያ እን​ዲ​ኖ​ሩህ ብት​ፈ​ልግ ግን በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ካሉት ከእ​ነ​ርሱ ከአ​ሕ​ዛብ ወን​ድና ሴት ባያ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ግዙ።


ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ታወ​ር​ሱ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ና​ንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ውርስ ይሆ​ናሉ፤ ነገር ግን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማና​ቸ​ውም ሰው ወን​ድ​ሙን በሥራ አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።


በየ​ዓ​መቱ እንደ ምን​ደኛ ከእ​ርሱ ጋር ይኑር፤ በፊ​ትህ እንደ ቀደ​መው አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እና​ን​ተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣ​ች​ሁን እያ​በ​ረ​ዳ​ችሁ፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር እያ​ላ​ችሁ፥ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ ፊት አይቶ የማ​ያ​ዳላ ጌታ በእ​ነ​ር​ሱና በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ማይ እንደ አለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


በመ​ን​ገድ ላይ እንደ ተቃ​ወ​መህ፥ አን​ተም ተር​በ​ህና ደክ​መህ ሳለህ ጓዝ​ህ​ንና ከአ​ንተ በኋላ ደክ​መው የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ራ​ውም።


ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


跟着我们:

广告


广告