Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 25:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አም​ሳ​ኛ​ው​ንም ዓመት ትቀ​ድ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ለሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ነጻ​ነ​ትን ታው​ጃ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስ​ቱና ወደ ወገኑ ይመ​ለስ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዐምሳኛውን ዓመት ቀድሱ፤ በምድሪቱ ሁሉ ላሉ ነዋሪዎች በሙሉ ነጻነት ዐውጁ፤ ይህም ኢዮቤልዩ ይሁንላችሁ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ ወደ ቤተ ሰቡ ርስት፣ ወደ ወገኑም ይመለስ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኀምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእንናተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለሳል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚህም ሁኔታ ኀምሳኛውን ዓመት ለይታችሁ በምድሪቱ ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ ከዚያ በፊት የተሸጠ ማናቸውም መሬት ለባለቤቱ ወይም ለዘሩ ይመለሳል፤ ባርያም ሆኖ ለማገልገል የተሸጠ ሰው ወደ ቤተሰቡ ይመለሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእንናተ ኢዮቤልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለስ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 25:10
30 交叉引用  

ከሕ​ዝቡ ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይውጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ረው አም​ላክ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ይሥራ፤


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ስ​ጋና ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በመ​ሰ​ንቆ ዘምሩ፤


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤


የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም፦ ውጡ፤ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን፦ ተገ​ለጡ፤ ትል ዘንድ።” በመ​ን​ገ​ድም ሁሉ ላይ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በጥ​ር​ጊያ ጎዳና ሁሉ ላይ ይሆ​ናል።


የም​በ​ቀ​ል​በት ቀን ደር​ሶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፥ የም​ቤ​ዥ​በ​ትም ዐመት ደር​ሶ​አ​ልና።


ሰው ሁሉ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ዛ​ቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለ​ቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አር​ነ​ትም አወ​ጡ​አ​ቸው።


ስለ አር​ነ​ታ​ቸው ዐዋጅ እን​ዲ​ነ​ግር ንጉሡ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከአ​ደ​ረገ በኋላ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።


ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ለአ​ንዱ ከር​ስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነፃ​ነት ዓመት ድረስ ለእ​ርሱ ይሁን፥ ከዚ​ያም በኋላ ለአ​ለ​ቃው ይመ​ለስ፤ ርስቱ ግን ለል​ጆቹ ይሁን።


ያ አም​ሳ​ኛው ዓመት ለእ​ና​ንተ ኢዮ​ቤ​ልዩ ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም አት​ዝሩ፤ የገ​ቦ​ው​ንም አት​ጨዱ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም በእ​ርሱ አት​ል​ቀሙ።


“በዚች ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመ​ለ​ሳል።


በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ከአ​ንተ ይወ​ጣል፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም፥ ወደ አባ​ቱም ርስት ይመ​ለ​ሳል።


በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይ​ቤዥ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ይውጣ።


ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ድነን ያለ ፍር​ሀት፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ባለ​በ​ትም በዚያ ነፃ​ነት አለ።


አጋ​ርም በዐ​ረብ ሀገር ያለች ደብረ ሲና ናት፤ ከዛ​ሬ​ዪቱ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ጋር ትነ​ጻ​ጸ​ራ​ለች፤ ከል​ጆ​ችዋ ጋርም ትገ​ዛ​ለች።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ።


አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።


跟着我们:

广告


广告