Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዕውር፥ ወይም ሰባራ፥ ወይም ምላሱ የተ​ቈ​ረጠ፥ ወይም የሚ​መ​ግል ቍስል ያለ​በት፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለእ​ሳት ቍር​ባን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር አታ​ሳ​ርጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም ማንኛውንም ዐይነት እከክ ወይም ቋቍቻ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ ከእነዚህ መካከል የትኛውንም በመሠዊያው ላይ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዓይነ ስውር ወይም የተሰበረ ወይም አካለ ጎዶሎ ወይም የሚመግል ቁስል ወይም የእከክ ደዌ ያለበት ወይም ቋቁቻ የወጣበት ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለጌታ አታቅርቡ፤ እነርሱንም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ በመሠዊያው ላይ ለጌታ አትሠዉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዕውር፥ ሰባራ ወይም ጉንድሽ የሆነ ወይም የሚመግል ቊስል፥ እከክ ወይም ሽፍታ ያለበት ማናቸውንም እንስሳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ እንደነዚህ ያሉትን እንስሶች በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበት ወይም እከካም ወይም ቍቍቻም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ እነዚህም ለእሳት ቍርባን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር አታሳርጉ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 22:22
9 交叉引用  

የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


ነገር ግን አይ​ሠ​ም​ር​ላ​ች​ሁ​ምና ነውር ያለ​በ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ።


ማና​ቸ​ውም ሰው ስእ​ለ​ቱን ለመ​ፈ​ጸም ወይም በፈ​ቃዱ ለማ​ቅ​ረብ የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢያ​ቀ​ርብ፥ ይሰ​ም​ር​ለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነው​ርም አይ​ሁ​ን​በት።


በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተ​ቈ​ረጠ ቢሆን፥ ቈጥ​ረህ የራ​ስህ ገን​ዘብ አድ​ር​ገው እንጂ ለስ​እ​ለት አይ​ቀ​በ​ል​ህም።


ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ባሉ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥


የአ​ሮ​ንም ልጆች ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያቀ​ር​ቡ​ታል፤ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ነው።


ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፣ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告