Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 22:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ማና​ቸ​ውም ሰው ስእ​ለ​ቱን ለመ​ፈ​ጸም ወይም በፈ​ቃዱ ለማ​ቅ​ረብ የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢያ​ቀ​ርብ፥ ይሰ​ም​ር​ለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነው​ርም አይ​ሁ​ን​በት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ማንኛውም ሰው ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ከላም ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት ሲያቀርብ፣ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ፍጹም የሆነውንና እንከን የሌለበትን ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ማናቸውም ሰው ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የአንድነትን መሥዋዕት ለጌታ ቢያቀርብ፥ እንዲሠምርለት ፍጹም የሆነ ይሁን፥ በእርሱም ነውር የሆነ ነገር አይኑርበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ማንም ሰው ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የአንድነት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ተቀባይነት ማግኘት እንዲችል፥ እንስሳው ምንም ነውር የሌለበት ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሠምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፥ ነውርም አይሁንበት።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 22:21
13 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ ብሎ ስእ​ለት ተሳለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በም​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ ቢጠ​ብ​ቀኝ፥ የም​በ​ላ​ው​ንም እን​ጀራ፥ የም​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ልብስ ቢሰ​ጠኝ፥


የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከደም አድ​ነኝ፥ አን​ደ​በ​ቴም በአ​ንተ ጽድቅ ደስ ይለ​ዋል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ያመጡ ዘንድ ልባ​ቸው ያስ​ነ​ሣ​ቸው ወን​ዶ​ችና ሴቶች ሁሉ ሙሴ ይሠራ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላዘ​ዘው ሥራ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አመጡ።


“የፍቅሬ መሥዋዕት ነው፤ ዛሬ ስእለቴን እሰጣለሁ።


ዕውር፥ ወይም ሰባራ፥ ወይም ምላሱ የተ​ቈ​ረጠ፥ ወይም የሚ​መ​ግል ቍስል ያለ​በት፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለእ​ሳት ቍር​ባን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር አታ​ሳ​ርጉ።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ቢሆን፥ ከላ​ሞች መንጋ ተባት ወይም እን​ስት ቢያ​ቀ​ርብ፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቅ​ርብ።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባኑ ከበ​ጎች ተባት ወይም እን​ስት ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ያቀ​ር​ባል።


በፈ​ቃ​ዳ​ች​ሁም ቢሆን በበ​ዓ​ላ​ች​ሁም ቢሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእ​ለ​ቱን አብ​ዝ​ታ​ችሁ በአ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።


ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ለሌላ መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ስእ​ለ​ትን ለመ​ፈ​ጸም፥ ወይም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከላም ወገን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ዘ​ጋጅ፥


跟着我们:

广告


广告