Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 19:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 “በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 “ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 “በዕድሜ የገፉ ሽማግሌዎች ሲመጡ ስታይ ከተቀመጥክበት በመነሣት አክብራቸው፤ እኔን አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 19:32
15 交叉引用  

እር​ስ​ዋም አባ​ቷን፥ “ጌታዬ በፊ​ትህ ለመ​ቆም ስላ​ል​ቻ​ልሁ የአ​ቀ​ለ​ል​ሁህ አይ​ም​ሰ​ልህ፤ በሴ​ቶች የሚ​ደ​ርስ ግዳጅ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና” አለ​ችው። ላባም የራ​ሔ​ልን ድን​ኳን በረ​በረ፤ ነገር ግን ጣዖ​ቶ​ቹን አላ​ገ​ኘም።


ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ።


ቤር​ሳ​ቤ​ህም የአ​ዶ​ን​ያ​ስን ነገር ትነ​ግ​ረው ዘንድ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ገባች፤ ንጉ​ሡም ሊቀ​በ​ላት ተነሣ፤ ሳማ​ትም፤ በዙ​ፋ​ኑም ተቀ​መጠ፤ ለን​ጉ​ሡም እናት ወን​በር አስ​መ​ጣ​ላት፤ በቀ​ኙም ተቀ​መ​ጠች።


ነገር ግን በታ​ላቅ ኀይል በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እር​ሱን ፍሩ፤ ለእ​ር​ሱም ስገዱ፤ ለእ​ር​ሱም ሠዉ።


ኤሊ​ዩስ ግን ከእ​ርሱ ይልቅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነበ​ሩና ለኢ​ዮብ መልስ ለመ​ስ​ጠት ጠብቆ ነበር።


የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ በዕ​ድ​ሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እና​ንተ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ናችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ዕው​ቀ​ቴን እገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።


መልካም ሽምግልና የክብር አክሊል ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል።


ለጐልማሶች ጌጣቸው ጥበብ ነው። ለሽማግሌዎችም ክብራቸው ሽበት ነው።


ልጄ ሆይ፥ የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።


ሕዝብ በሕ​ዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይገ​ፋ​ፋል፤ ብላ​ቴ​ና​ውም በሽ​ማ​ግ​ሌው ላይ፥ የተ​ጠ​ቃ​ውም በከ​በ​ር​ቴው ላይ ይታ​በ​ያል።


አለ​ቆች በእ​ጃ​ቸው ተሰ​ቀሉ፤ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም ፊት አላ​ከ​በ​ሩም።


ደን​ቆ​ሮ​ውን አት​ስ​ደብ፤ በዕ​ው​ርም ፊት ዕን​ቅ​ፋት አታ​ድ​ርግ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ለሁ​ሉም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው አድ​ርጉ፤ ግብር ለሚ​ገ​ባው ግብ​ርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚ​ገ​ባው ቀረ​ጥን ስጡ፤ ዐሥ​ራት ለሚ​ገ​ባው ዐሥ​ራ​ትን ስጡ፤ ሊፈ​ሩት የሚ​ገ​ባ​ውን ፍሩ፤ ክብር የሚ​ገ​ባ​ው​ንም አክ​ብሩ።


ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፤ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፥ ቆነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና ለምናቸው።


ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


跟着我们:

广告


广告