Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 19:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሰው ቢሞት ምላጭ ወደ ሥጋ​ችሁ አታ​ቅ​ርቡ፤ ገላ​ች​ሁ​ንም አት​ን​ቀ​ሱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 “ ‘ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትንጩ፤ በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ስለ ሞተውም ብላችሁ ሥጋችሁን አትተልትሉ፥ ገላችሁንም ፈጽሞ አትንቀሱት፤ እኔ ጌታ ነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በሰውነታችሁ ላይ ንቅሳት አታድርጉ፤ ወይም ለሙታን በማዘን ሰውነታችሁን አትቈራርጡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 19:28
18 交叉引用  

በታ​ላ​ቅም ቃል ይጮኹ ጀመር፤ እንደ ልማ​ዳ​ቸ​ውም ደማ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ስስ ድረስ ገላ​ቸ​ውን በጦ​ርና በሰ​ይፍ ይብ​ዋ​ጭሩ ነበር።


ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፥ አይ​ቀ​በ​ሩም ሰዎ​ችም አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ፊት አይ​ነ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ ራስ​ንም አይ​ላ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤


በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃ​ነት አለ፤ ጽሕ​ማ​ቸ​ውን ሁሉ ይላ​ጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ሁሉም በወ​ገ​ባ​ቸው ማቅን ይታ​ጠ​ቃሉ።


የራስ ጠጕ​ራ​ች​ሁ​ንም ዙሪ​ያ​ውን አት​ከ​ር​ክ​ሙት፤ ጢማ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ።


“ምድ​ሪቱ ከግ​ል​ሙ​ትና፥ ከር​ኵ​ሰ​ትም እን​ዳ​ት​ሞላ ሴት ልጅ​ህን ታመ​ነ​ዝር ዘንድ አታ​ር​ክ​ሳት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፥ “ከወ​ገ​ና​ቸው በሞተ ሰው ራሳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለካ​ህ​ናቱ ለአ​ሮን ልጆች ንገ​ራ​ቸው።


ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይ​ግባ፤ በአ​ባ​ቱም ወይም በእ​ናቱ አይ​ር​ከስ።


ስለ ሞተው ሰው ራሳ​ቸ​ውን አይ​ላጩ፤ ጢማ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም አይ​ንጩ።


ሁልጊዜም ሌሊትና ቀን በመቃብርና በተራራ ሆኖ ይጮኽ ነበር፤ ሰውነቱንም በድንጋይ ይቧጭር ነበር።


ሌሎች ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም፥ “ጌታ​ች​ንን አየ​ነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የች​ን​ካ​ሩን ምል​ክት በእጁ ካላ​የሁ፥ ጣቴ​ንም ወደ ተቸ​ነ​ከ​ረ​በት ካል​ጨ​መ​ርሁ፥ እጄ​ንም ወደ ጎኑ ካላ​ገ​ባሁ አላ​ም​ንም” አላ​ቸው።


“ለሞተ ሰውም በዐ​ይ​ና​ችሁ መካ​ከል ፊታ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ፤


የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”


ሦስተኛም መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥


በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፤ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።


ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።


跟着我们:

广告


广告