Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 16:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ለመ​ለ​ቀቅ የሚ​ሆ​ነ​ውን ፍየል የወ​ሰደ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “የሚለቀቀውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰፈር መግባት ይችላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወደ ዐዛዜል የሄደውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የተመረጠውን ፍየል እየነዳ ወደ በረሓ ይዞት ሄዶ የነበረውም ሰው ወደ ሰፈር ከመግባቱ በፊት ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም ይታጠብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ለመለቀቅ የሚሆነውን ፍየል የወሰደ ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 16:26
19 交叉引用  

“በእ​ነ​ዚ​ህም ርኩስ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድን የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


በአ​ራት እግ​ሮቹ ከሚ​ሄድ እን​ስሳ ሁሉ በመ​ዳ​ፎቹ ላይ የሚ​ሄድ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ የእ​ር​ሱን በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


በድ​ና​ቸ​ው​ንም የሚ​ያ​ነሣ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። እነ​ር​ሱም በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን ናቸው።


ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱት ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸው በም​ንም ላይ ቢወ​ድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕ​ን​ጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍር​በት ወይም ከረ​ጢት ቢሆን የሚ​ሠ​ራ​በት ዕቃ ሁሉ እር​ሱን በውኃ ውስጥ ይን​ከ​ሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


“ለመ​ብል ከሚ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ እን​ስ​ሳት የሞተ ቢኖር፥ በድ​ኑን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከበ​ድ​ኑም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ በድ​ኑ​ንም የሚ​ያ​ነሣ፤ ልብ​ሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብ​ሱ​ንም ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


የመ​ለ​ቀ​ቅም ዕጣ የሆ​ነ​በ​ትን ፍየል ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​በት ዘንድ፥ ለመ​ለ​ቀ​ቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደው ዘንድ በሕ​ይ​ወቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​መ​ዋል።


የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ያቃ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል።


አሮ​ንም በሁ​ለቱ የፍ​የል ጠቦ​ቶች ላይ ዕጣ ይጥ​ል​ባ​ቸ​ዋል፤ አን​ዱን ዕጣ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ሌላ​ው​ንም ዕጣ ለሚ​ለ​ቀቅ።


ይህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ውን ውኃ የሚ​ረጭ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ የሚ​ያ​ነ​ጻ​ው​ንም ውኃ የሚ​ነካ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።


ኦሪት ምንም ግዳጅ አል​ፈ​ጸ​መ​ች​ምና፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ፋንታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ን​ቀ​ር​ብ​በት ከእ​ር​ስዋ የሚ​ሻል ተስፋ ገብ​ቶ​አል።


跟着我们:

广告


广告