Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 16:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍራ ገላ​ውን በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ሌላ​ው​ንም ልብስ ለብሶ ይወ​ጣል፤ የእ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ለካ​ህ​ናቱ እን​ዳ​ስ​ተ​ሰ​ረየ ለራ​ሱም፥ ለሕ​ዝ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ለሕዝቡም ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ይለብሳል፤ ወጥቶም ለእርሱ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት እና ለሕዝቡ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በተቀደሰውም ቦታ ሰውነቱን ታጥቦ የዘወትር ልብሱን ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ የራሱንና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የሕዝቡንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 16:24
14 交叉引用  

ለአ​ሮ​ንም ልጆች የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ችን፥ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ዎ​ች​ንም፥ ቆቦ​ች​ንም ለክ​ብ​ርና ለመ​ለያ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ይህ​ንም ሁሉ ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታነ​ጻ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ።


ካህ​ና​ቱም በገቡ ጊዜ ከመ​ቅ​ደሱ በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አይ​ወ​ጡም፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖ​ሩ​ታል፤ ሌላም ልብስ ለብ​ሰው ወደ ሕዝብ ይወ​ጣሉ።”


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ጠጕ​ሩን ሁሉ ይላ​ጫል፤ ራሱ​ንም፥ ጢሙ​ንም፥ ቅን​ድ​ቡ​ንም፥ የገ​ላ​ው​ንም ጠጕር ሁሉ ይላ​ጫል፤ ልብ​ሱ​ንም፥ ገላ​ው​ንም በውኃ ያጥ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።


የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


እነ​ዚ​ህን ሁሉ የሚ​ነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ገላ​ውን በውኃ ካል​ታ​ጠበ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ወደ መሠ​ዊ​ያው ቀር​በህ የኀ​ጢ​አ​ት​ህን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን ሠዋ፤ ለራ​ስ​ህና ለወ​ገ​ንህ አስ​ተ​ስ​ርይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘዘ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቅ​ርብ፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም” አለው።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告