Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 “እን​ዲ​ሁም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ያለ​ች​ውን ድን​ኳ​ኔን ባረ​ከሱ ጊዜ፥ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሞቱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው አን​ጹ​አ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “ ‘በመካከላቸው ያለችውን ማደሪያዬን እንዳያረክሱና በርኩሰታቸው እንዳይሞቱ፣ እስራኤላውያንን ከሚያረክሳቸው ነገር ለዩአቸው።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 “እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “በመካከላቸው ያለውን ማደሪያዬን በማርከስ እንዳይሞቱ እስራኤላውያንን ከርኲሰት ጠብቃቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ማደሪያዬን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለያቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 15:31
22 交叉引用  

ይህን ደግሞ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ኛል፤ በዚያ ቀን መቅ​ደ​ሴን አር​ክ​ሰ​ዋል፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ሽረ​ዋል።


“የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በም​ድ​ራ​ቸው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በጣ​ዖ​ታ​ቸው አረ​ከ​ሱ​አት፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በፊቴ እንደ አደፍ ርኵ​ሰት ነበረ።


በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው።


ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእ​ድ​ፍ​ሽና በር​ኵ​ሰ​ትሽ መቅ​ደ​ሴን ስላ​ረ​ከ​ስሽ፥ ስለ​ዚህ በእ​ው​ነት እኔ አሳ​ን​ስ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም።


በር​ኩ​ስና በን​ጹሕ መካ​ከል፥ የሕ​ይ​ወት ነፍስ ካላ​ቸ​ውም በም​ት​በ​ሉ​ትና በማ​ት​በ​ሉት መካ​ከል እን​ድ​ት​ለዩ ነው።”


“በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተ​ልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለ​ምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”


“ፈሳሽ ነገር ላለ​በት ሰው፥ ይረ​ክ​ስም ዘንድ ዘሩ ለሚ​ወ​ጣ​በት ሰው፥


ሰን​በ​ታ​ቴን ጠብቁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም አክ​ብሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


መቅ​ደ​ሴን ያረ​ክስ ዘንድ፥ የቅ​ዱ​ሳ​ኔ​ንም ስም ያጐ​ስ​ቍል ዘንድ ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ሰጥ​ቶ​አ​ልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከ​ብ​ዳ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን ነው​ረኛ ነውና መቅ​ደ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​ረ​ክስ ወደ መጋ​ረ​ጃው አይ​ግባ፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም አይ​ቅ​ረብ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


የሞ​ተ​ውን ሰው በድን የነካ ሁለ​መ​ና​ውን ባያ​ነጻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን ያረ​ክ​ሳል፤ ያ ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በእ​ር​ሱም ላይ የሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ይሆ​ናል፤ ርኵ​ሰቱ ገና በእ​ርሱ ላይ ነው።


“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለ​መ​ና​ው​ንም ባያ​ነጻ፥ ያ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ አር​ክ​ሶ​አ​ልና ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ በሚ​ያ​ነጻ ውኃ አል​ተ​ረ​ጨ​ምና ርኩስ ነው።


እኔ በመ​ካ​ከሉ የማ​ድ​ር​በ​ትን ሰፈ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ከወ​ንድ እስከ ሴት ከሰ​ፈሩ አው​ጡ​አ​ቸው።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ የሚ​ያ​ፈ​ር​ሰ​ውን ግን እር​ሱን ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያፈ​ር​ሰ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስም እና​ንተ ራሳ​ችሁ ናችሁ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ አታ​ር​ክሱ።


“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ የከዳ፥ ያን​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​በ​ትን የኪ​ዳ​ኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈ​ጠረ፥ የጸ​ጋ​ው​ንም መን​ፈስ ያክ​ፋፋ እን​ዴት ይልቅ የሚ​ብስ ቅጣት የሚ​ገ​ባው ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል?


ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


ስለ​ዚ​ህም የዔሊ ቤት ኀጢ​አት በዕ​ጣ​ንና በመ​ሥ​ዋ​ዕት ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ሰ​ረ​ይ​ለት ለዔሊ ቤት ምያ​ለሁ።”


跟着我们:

广告


广告