Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሹ በእግዚአብሔር ፊት ለሰውየው ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ካህኑም ከእነርሱ አንዱን ኃጢአት የሚሰረይበት መሥዋዕት፥ ሌላውንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 15:15
22 交叉引用  

“በእ​ነ​ዚ​ህም ርኩስ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድን የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


በአ​ራት እግ​ሮቹ ከሚ​ሄድ እን​ስሳ ሁሉ በመ​ዳ​ፎቹ ላይ የሚ​ሄድ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ የእ​ር​ሱን በድን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


በድ​ና​ቸ​ው​ንም የሚ​ያ​ነሣ ልብ​ሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። እነ​ር​ሱም በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን ናቸው።


ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱት ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸው በም​ንም ላይ ቢወ​ድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕ​ን​ጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍር​በት ወይም ከረ​ጢት ቢሆን የሚ​ሠ​ራ​በት ዕቃ ሁሉ እር​ሱን በውኃ ውስጥ ይን​ከ​ሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


“ለመ​ብል ከሚ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ እን​ስ​ሳት የሞተ ቢኖር፥ በድ​ኑን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


ከበ​ድ​ኑም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ በድ​ኑ​ንም የሚ​ያ​ነሣ፤ ልብ​ሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ት​ማል፤ ከደ​ም​ዋም ፈሳሽ ትነ​ጻ​ለች። ወንድ ወይም ሴት ለም​ት​ወ​ልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው።


ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”


እን​ዲ​ህም በወ​ይ​ፈኑ ያደ​ር​ጋል፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት በታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ አደ​ረገ እን​ዲሁ በዚህ ያደ​ር​ጋል፤ ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።


ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


ስቡም ሁሉ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ፥ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ እርሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


ስቡ ሁሉ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው የበግ ጠቦት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


ካህ​ኑም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ባለ​ማ​ወቅ ነበ​ርና ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውና ስላ​ለ​ማ​ወ​ቃ​ቸው ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባሉ።


ለአ​ም​ላኩ ቀን​ቶ​አ​ልና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ስ​ር​ዮ​አ​ልና፥ ለእ​ርሱ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የክ​ህ​ነት ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ለ​ታል።”


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


跟着我们:

广告


广告