Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በካ​ህ​ኑም እጅ ውስጥ የቀ​ረ​ውን ዘይት ካህኑ በሚ​ነ​ጻው ሰው ራስ ላይ ያደ​ር​ግ​በ​ታል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ካህኑም በመዳፉ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያድርግ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያስተስርይለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ካህኑም በእጁ መዳፍ ላይ የተረፈውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርግበታል፤ ከዚያም ካህኑ በጌታ ፊት ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በእጁ መዳፍ ላይ የተረፈውንም ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስሰው፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በካህኑም እጅ ውስጥ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርግበታል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 14:18
13 交叉引用  

የቅ​ብ​ዐ​ት​ንም ዘይት ወስ​ደህ በራሱ ላይ ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ው​ማ​ለህ።


ካህ​ኑም በእጁ ውስጥ ከቀ​ረው ዘይት የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ባረ​ፈ​በት ላይ ይቀ​ባ​ዋል።


ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


እን​ዲ​ህም በወ​ይ​ፈኑ ያደ​ር​ጋል፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት በታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ አደ​ረገ እን​ዲሁ በዚህ ያደ​ር​ጋል፤ ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።


ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


ስቡም ሁሉ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ፥ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ እርሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


ስቡ ሁሉ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው የበግ ጠቦት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት በተ​ቃ​ጠ​ለው ቍር​ባን ላይ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


በተ​ቀ​ደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኀጢ​አት ዕዳ ይከ​ፍ​ላል፤ አም​ስ​ተ​ኛ​ው​ንም እጅ ይጨ​ም​ር​በ​ታል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል። ካህ​ኑም በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


ከቅ​ብ​ዐ​ቱም ዘይት በአ​ሮን ራስ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ቀባው፤ ቀደ​ሰ​ውም።


ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


跟着我们:

广告


广告