Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ካህ​ኑም ከበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ይቀ​ባ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ካህኑ ከበደል መሥዋዕቱ ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ታችኛውን ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ካህኑም ከበደል መሥዋዕት ደም ይወስዳል፤ እርሱም የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት ያስነካዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ካህኑም ከጠቦቱ ደም ጥቂት ወስዶ የነጻ መሆኑን በሚያስታውቅለት ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንና የቀኝ እግሩን አውራ ጣቶች ይቀባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ካህኑም ከበደል መሥዋዕት ደም ወስዶ የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት ያስነካዋል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 14:14
16 交叉引用  

አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የአ​ሮ​ን​ንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንና የቀኝ እግ​ሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የል​ጆ​ቹ​ንም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንና የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ውን አውራ ጣት ታስ​ነ​ካ​ለህ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።


እን​ግ​ዲህ በበ​ደል ላይ በደል እየ​ጨ​መ​ራ​ችሁ ለምን ትቀ​ሠ​ፋ​ላ​ችሁ? ራስ ሁሉ ለሕ​ማም፥ ልብም ሁሉ ለኀ​ዘን ሆኖ​አል።


ካህ​ኑም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ ለማ​ን​ጻት ለሚ​ነ​ጻው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከዚ​ህም በኋላ ካህኑ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዳል።


የበ​ደ​ሉ​ንም መሥ​ዋ​ዕት የበግ ጠቦት ያር​ዳል፤ ካህ​ኑም ከበ​ደሉ መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ይቀ​ባ​ዋል።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ውና ቅዱስ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ርቡ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርኅ​ራኄ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ይህም በዕ​ው​ቀት የሚ​ሆን አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ነው።


ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጉ እንጂ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት የዐ​መፅ የጦር መሣ​ሪያ አታ​ድ​ር​ጉት፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ የጦር መሣ​ሪያ አድ​ርጉ።


ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ።


በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


跟着我们:

广告


广告