Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ካህኑ ያየ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ በቋ​ቁ​ቻው ጠጕሩ ተለ​ውጦ ቢነጣ፥ ወደ ቆዳ​ውም ውስጥ ቢጠ​ልቅ፥ ለምጽ ነው፤ ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ስፍራ ወጥ​ቶ​አል፤ ካህ​ኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ የለ​ምጽ ደዌ ነውና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ካህኑ ይመርምረው፤ ቋቍቻው ባለበትም ቦታ ያለው ጠጕር ቢነጣና ከቈዳው በታች ዘልቆ ቢገባ፣ በቃጠሎው ሰበብ ከውስጥ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፤ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ካህኑ ያየዋል፥ እነሆም፥ በቋቁቻው ላይ ያለው ጠጉር ተለውጦ ቢነጣ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ቢታይ፥ የለምጽ ደዌ ነው፤ ከተቃጠለውም ስፍራ ወጥቶአል፤ ካህኑም፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ካህኑ ይመርምረው፤ ቊስሉ ባለበት ስፍራ የበቀለው ጠጒር ነጭ ቢሆንና ያም ስፍራ በዙሪያው ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ከተገኘ፥ ከእሳት ቃጠሎ የመጣ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ስለዚህም ካህኑ ያ ሰው የረከሰ መሆኑን ያስታውቅ። ይህም የሥጋ ደዌ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ካህኑ ያየዋል፥ እነሆም፥ በቍቁቻው ጠጕሩ ተለውጦ ቢነጣ፥ ወደ ቁርበቱም ውስጥ ቢጠልቅ፥ ለምጽ ነው፤ ከተቃጠለውም ስፍራ ወጥቶአል፤ ካህኑም፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 13:25
7 交叉引用  

ነገር ግን የን​ዕ​ማን ለምጽ በአ​ን​ተና በዘ​ርህ ላይ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ” አለው። እንደ በረ​ዶም ለም​ጻም ሆኖ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።


ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ አግባ አለው።” እጁ​ንም ወደ ብብቱ አገ​ባት፤ “እጅ​ህ​ንም ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ እጁም ለምጽ ሆነች።


“በሥ​ጋ​ውም ቆዳ የእ​ሳት ትኩ​ሳት ቢኖ​ር​በት፥ በተ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ስፍራ ነጭ፥ ወይም ቀላ ያለ ቋቍቻ ቢታይ፥


ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ በቋ​ቍ​ቻ​ውም ነጭ ጠጕር ባይ​ኖር፥ ወደ ቆዳ​ውም ባይ​ጠ​ልቅ፥ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


ቋቍ​ቻ​ውም በሥ​ጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆ​ዳ​ውም የጠ​ለቀ ባይ​መ​ስል፥ ጠጕ​ሩም ባይ​ነጣ፥ ካህኑ የታ​መ​መ​ውን ሰው ሰባት ቀን ይዘ​ጋ​በ​ታል።


ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ ተነሣ፤ እነ​ሆም፥ ማር​ያም ለም​ጻም ሆነች፤ እንደ በረ​ዶም ነጭ ሆነች፤ አሮ​ንም ማር​ያ​ምን ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ለም​ጻም ሆና ነበር።


跟着我们:

广告


广告