Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ነ​ዚ​ህን ሥጋ አት​በ​ሉም፤ በድ​ና​ቸ​ው​ንም አት​ነ​ኩም፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ፤ ጥንባቸውንም አትንኩ፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ለእናንተ የረከሱ ስለ ሆኑ እነዚህን እንስሶች አትብሉ፤ በድናቸውንም እንኳ አትንኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 11:8
22 交叉引用  

እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድር ላይ አይ​ቀ​መ​ጡም፤ ኤፍ​ሬ​ምም በግ​ብፅ ይቀ​መ​ጣል፤ በአ​ሦ​ርም ርኩስ ነገ​ርን ይበ​ላሉ።


እር​ያም ሰኰ​ናው ተሰ​ን​ጥ​ቆ​አል፤ ነገር ግን ስለ​ማ​ያ​መ​ሰኳ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።


“በውኃ ውስጥ ከሚ​ኖ​ሩት ሁሉ እነ​ዚ​ህን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በው​ኆች፥ በባ​ሕ​ሮ​ችም፥ በወ​ን​ዞ​ችም ውስጥ ከሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ክን​ፍና ቅር​ፊት ያላ​ቸ​ውን ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


ርኩስ ነገ​ርን፥ የሞ​ተ​ውን፥ አውሬ የነ​ከ​ሰ​ውን፥ ወይም የበ​ከተ፥ ወይም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የእ​ን​ስ​ሳን በድን የነካ፥ ከእ​ር​ሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤


ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፤” አላቸው።


ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።”


ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።


እርሱም “እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?


ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ።


ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ ሰው ሄዶ ከባ​ዕድ ወገን ጋር መቀ​ላ​ቀል እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ባው ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማን​ንም ቢሆን እን​ዳ​ል​ጸ​የ​ፍና ርኩስ ነው እን​ዳ​ልል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​የኝ።


ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


ለወ​ን​ድም ዕን​ቅ​ፋት ከመ​ሆን ሥጋን አለ​መ​ብ​ላት ወይ​ን​ንም አለ​መ​ጠ​ጣት ይሻ​ላል።


መብል ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ደ​ር​ሰ​ንም፤ ብን​በ​ላም አይ​ረ​ባ​ንም፤ ባን​በ​ላም አይ​ጎ​ዳ​ንም።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


የሥራ ፍሬ ከሌ​ላ​ቸው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ቸ​ውም ጨለማ ከሆነ ሰዎች ጋር አት​ተ​ባ​በሩ፤ ገሥ​ጹ​አ​ቸው እንጂ።


እን​ግ​ዲህ አት​ም​ሰ​ሉ​አ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告