Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸው በም​ንም ላይ ቢወ​ድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕ​ን​ጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍር​በት ወይም ከረ​ጢት ቢሆን የሚ​ሠ​ራ​በት ዕቃ ሁሉ እር​ሱን በውኃ ውስጥ ይን​ከ​ሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በድኑ በማንኛውም ዕቃ ላይ ቢወድቅ ያ ዕቃ ከዕንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቈዳ ወይም ከበርኖስ የተሠራ ከረጢት ቢሆን ርኩስ ይሆናል፤ በውሃ ውስጥ ይደረግ፤ ሆኖም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከእነርሱም የሞተው በማናቸውም ነገር ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቆዳ ወይም ከረጢት ቢሆን ለማናቸውም ሥራ የሚጠቅም ዕቃ ሁሉ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ግን ይነጻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በድናቸው የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ይረክሳል፤ ይኸውም ከእንጨት የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ልብስን፥ ቆዳን ወይም ከረጢት የመሳሰሉትንና ሌላውንም ነገር ሁሉ ይጨምራል፤ የእነርሱ በድን የነካው ይህን የመሰለ ዕቃ ሁሉ በውሃ ውስጥ ተነክሮ ይቈይ፤ እስከ ምሽትም ድረስ ርኩስ ሆኖ ከዚያ በኋላ ንጹሕ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከእነርሱም የሞተው በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቁርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 11:32
12 交叉引用  

ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱት ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ርኩ​ሳን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።


በተ​ዘ​ጋ​በ​ትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚ​ገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።


ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው የሚ​ነ​ካ​ውን የሸ​ክላ ዕቃ ይስ​በ​ሩት፤ የዕ​ን​ጨ​ቱ​ንም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይጠ​ቡት፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።


ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


ለመ​ለ​ቀቅ የሚ​ሆ​ነ​ውን ፍየል የወ​ሰደ ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል።


የሞ​ተ​ውን ወይም አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን የሚ​በላ ሰው ሁሉ፥ የሀ​ገር ልጅ ወይም እን​ግዳ ቢሆን፥ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


እነ​ዚ​ህን ሁሉ የሚ​ነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ገላ​ውን በውኃ ካል​ታ​ጠበ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።


የሚ​ቀ​ቀ​ል​በ​ትን ሸክላ ይሰ​ብ​ሩ​ታል፤ በና​ስም ዕቃ ቢቀ​ቀል ይፈ​ገ​ፍ​ጉ​ታል፤ በው​ኃም ያጥ​ቡ​ታል።


መክ​ደ​ኛው ያል​ታ​ሰረ የተ​ከ​ፈተ ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።


ካህ​ኑም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውሃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል፤ ካህ​ኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆ​ናል።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


跟着我们:

广告


广告