Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከዎ​ፎች ቢሆን፥ ቍር​ባ​ኑን ከዋ​ኖስ ወይም ከር​ግብ ያቀ​ር​ባል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘ለእግዚአብሔር በሚቃጠል መሥዋዕትነት የሚቀርበው መባ ከወፎች ወገን ከሆነ፣ ዋኖስ ወይም የርግብ ጫጩት ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ለጌታም የሚቀርበው ቁርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከወፎች ቢሆን፥ ቁርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሰውየው፥ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ የፈለገው መባ ከወፎች ወገን ከሆነም የርግብ ጫጩት ወይም ዋኖስ መሆን ይችላል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለእግዚአብሔርም የሚቀርበው ቍርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከወፎች ቢሆን፥ ቍርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 1:14
10 交叉引用  

እር​ሱም አለው፥ “የሦ​ስት ዓመት ላም፥ የሦ​ስት ዓመት ፍየ​ልም፥ የሦ​ስት ዓመት በግም፥ ዋኖ​ስም፥ ርግ​ብም አምጣ፤ እኒ​ህ​ንም ሁሉ አም​ጥ​ተህ ከሁ​ለት ከሁ​ለት ቍረ​ጣ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው።”


ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”


እንደ ሥር​ዐ​ቱም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያዘ​ጋ​ጀ​ዋል። ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ስለ እርሱ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ያቀ​ር​ቡ​ለት ዘንድ።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


跟着我们:

广告


广告