ሰቈቃወ 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመለኪያውንም ገመድ ዘረጋ፤ እርስዋን ከማጥፋት እጁን አልመለሰም፤ ምሽጉና ቅጥሩ አለቀሱ፤ በአንድነትም ደከሙ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በጽዮን ሴት ልጅ ዙሪያ ያለውን ቅጥር፣ እግዚአብሔር ለማፍረስ ወሰነ፤ የመለኪያ ገመድ ዘረጋ፤ ከማጥፋትም እጆቹን አልሰበሰበም፤ ምሽጎችና ቅጥሮች እንዲያለቅሱ አደረገ፤ በአንድነትም ጠፉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ አሰበ፥ የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ እጁን ከማጥፋት አልመለሰም፥ ምሽጉና ቅጥሩ እንዲያለቅሱ አደረገ፥ በአንድነት ደከሙ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ አሰበ፥ የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ እጁን ከማጥፋት አልመለሰም፥ ምሽጉና ቅጥሩ እንዲያለቅሱ አደረገ፥ በአንድነት ደከሙ። 参见章节 |