ሰቈቃወ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ጋሜል። በጽኑ ቍጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፤ ቀኝ እጁንም ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፤ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ በላ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በጽኑ ቍጣው፣ የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ሰበረ፤ ጠላት በተቃረበ ጊዜ፣ ቀኝ እጁን ወደ ኋላ መለሰ፤ በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ እሳት፣ በያዕቆብ ላይ የእሳት ነበልባል ነደደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጋሜል። በጽኑ ቁጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፥ ቀኝ እጁን ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያውም እንደሚባላ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በኀይለኛ ቊጣው የእስራኤልን ኀይል ሁሉ አዳከመ፤ ጠላትም እያየ ለእነርሱ የሚሰጠውን ድጋፍ አቋርጦ፥ በያዕቆብም ዘር ላይ እንደሚንበለበል እሳት ቊጣውን አቀጣጠለ፤ ቊጣው ጐረቤቶቹንም ሁሉ አወደመ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ጋሜል። በጽኑ ቍጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፥ ቀኝ እጁን ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያውም እንደሚባላ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ። 参见章节 |