Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ታው። የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝን እንደ በዓል ቀን ከዙ​ሪ​ያዬ ጠራ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ቀንም ያመ​ለጠ ወይም የቀረ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ያቀ​ማ​ጠ​ል​ኋ​ቸ​ው​ንና ያሳ​ደ​ግ​ኋ​ቸ​ውን ጠላቴ በላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “በበዓል ቀን ለግብዣ እንደምትጠራ፣ ሽብርን ከየአቅጣጫው በእኔ ላይ ጠራህ፤ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ማንም አላመለጠም ወይም አልተረፈም፤ የተንከባከብኋቸውንና ያሳደግኋቸውን፣ ጠላቴ አጠፋብኝ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ታው። እንደ በዓል ቀን የሚያስፈሩኝን ከዙሪያዬ ጠራህ፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፥ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የበዓል ቀን ይመስል ጠላቶቼን ከየቦታው ጋብዘሃል፤ በቊጣህ ቀን አንድም ያመለጠ ወይም በሕይወት የተረፈ የለም፤ ወልጄ ያሳደግኋቸውን ጠላቴ ፈጃቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ታው። እንደ በዓል ቀን የሚያስፈሩኝን ከዙሪያዬ ጠራህ፥ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፥ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 2:22
16 交叉引用  

ስለ​ዚ​ህም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ንጉሥ አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ እር​ሱም ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን በቤተ መቅ​ደሱ ውስጥ በሰ​ይፍ ገደ​ላ​ቸው፤ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም አል​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ደና​ግ​ሉ​ንም አል​ማ​ረም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰ​ዳ​ቸው፤ ሁሉ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው።


ባለ​ፈም ጊዜ ይወ​ስ​ዳ​ች​ኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያል​ፋል፤ በሌ​ሊት ክፉ ተስፋ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ያዘ​ና​ችሁ፥ መስ​ማ​ትን ተማሩ።”


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያ​መ​ል​ጡት የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እኔም ይጮ​ኻሉ፤ እኔ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


በውኑ ይሁ​ዳን ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ዋ​ልን? ነፍ​ስ​ህስ ጽዮ​ንን ጠል​ታ​ታ​ለ​ችን? ስለ ምን መታ​ኸን? ፈው​ስስ ስለ ምን የለ​ንም? ስለ ምን ተስፋ አደ​ረ​ግን? ነገር ግን መል​ካም ነገር አል​ተ​ገ​ኘም፤ የፈ​ው​ስን ጊዜ ተስፋ አደ​ረ​ግን፤ ነገር ግን ድን​ጋጤ ሆነ።


በነ​ጋ​ውም ጳስ​ኮር ኤር​ም​ያ​ስን ከአ​ዘ​ቅት ውስጥ አወ​ጣው። ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም​ህን፦ ዘዋሪ ስደ​ተኛ እንጂ ጳስ​ኮር ብሎ አይ​ጠ​ራ​ህም።


ከዚህ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ ከቸ​ነ​ፈ​ርና ከሰ​ይፍ፥ ከራ​ብም በዚ​ህች ከተማ የቀ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡ​ንም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ሹት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም በሰ​ይፍ ስለት ይመ​ታ​ቸ​ዋል፤ አያ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ም​ራ​ቸ​ውም።”


“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


ፈር​ተው ወደ ኋላ ሲመ​ለሱ፥ ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሲደ​ክሙ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ሳይ​መ​ለ​ከቱ ፈጥ​ነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ይከ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የጠ​ላት ሰይፍ ከብ​በ​ዋ​ች​ኋ​ልና ወደ ሜዳ አት​ውጡ፤ በመ​ን​ገ​ድም ላይ አት​ሂዱ።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ርጉ​ማን ይሆ​ናሉ።


跟着我们:

广告


广告