Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ካፍ። ሕፃ​ኑና ጡት የሚ​ጠ​ባው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእ​ንባ ደከ​መች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በም​ድር ላይ ተዋ​ረደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሕዝቤ ስለ ተፈጀ፥ ሕፃናት በከተማይቱ መንገዶች ላይ ስለሚዝለፈለፉ፥ ዐይኖቼ በለቅሶ ደከሙ፤ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ፤ ተስፋም ቈረጥሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 2:11
26 交叉引用  

ተዘ​ልዬ ስኖ​ርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕ​ሬን ይዞ ነጨው፤ እንደ ዓላ​ማም አድ​ርጎ አቆ​መኝ፤ እንደ ጉበ​ኛም ተመ​ለ​ከ​ተኝ።


ሆዴ ፈላች፥ አላ​ረ​ፈ​ች​ምም፤ የች​ግ​ርም ዘመን መጣ​ች​ብኝ።


ወደ አንተ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ በል​ባ​ብና በል​ጓም ጉን​ጫ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ለ​ጕ​ሙ​አ​ቸው፥ ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው እንደ ፈረ​ስና እንደ በቅሎ አት​ሁኑ።


ከኀ​ጢ​አቴ ሁሉ አዳ​ን​ኸኝ፥ ለሰ​ነ​ፎ​ችም ስድብ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።


ዐይኔ ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፤ ከጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ የተ​ነሣ አረ​ጀሁ።


እሰይ! እሰይ! የሚ​ሉኝ አፍ​ረው ወዲ​ያው ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ።


ስለ​ዚህ፥ “ተዉኝ እኔ መራራ ልቅሶ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋ​ትም ታጽ​ና​ኑኝ ዘንድ አት​ድ​ከሙ፥” አልሁ።


እንደ ሸመላ እን​ዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግ​ብም አጕ​ረ​መ​ረ​ምሁ፤


ልጆ​ችሽ ዝለ​ዋል፤ እንደ ጠወ​ለገ ቅጠ​ልም በየ​መ​ን​ገዱ ዳር ወድ​ቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣና ተግ​ሣጽ ተሞ​ል​ተ​ዋል።


“እን​ደ​ዚ​ህም ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የወ​ገኔ ልጅ ድን​ግ​ሊቱ በታ​ላቅ ስብ​ራ​ትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ ሌሊ​ትና ቀን ሳያ​ቋ​ርጡ እን​ባን ያፍ​ስሱ።


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


“አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከይ​ሁዳ ወገን መካ​ከል ቅሬታ እን​ዳ​ይ​ቀ​ር​ላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ንና ሴትን፥ ብላ​ቴ​ና​ንና የሚ​ጠባ ሕፃ​ንን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራ​ሳ​ችሁ ላይ ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?


እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የለ​ምን? ወይስ ንጉ​ሥዋ በእ​ር​ስዋ ዘንድ የለ​ምን? የሚል የወ​ገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተ​ቀ​ረፁ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውና በባ​ዕድ ከን​ቱ​ነ​ትስ ያስ​ቈ​ጡኝ ስለ ምን​ድን ነው?


ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።


ዔ። የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ፥ ነፍ​ሴ​ንም የሚ​መ​ል​ሳት ከእኔ ርቆ​አ​ልና ዐይኔ ውኃ ያፈ​ስ​ሳል። ጠላት በር​ት​ቶ​አ​ልና ልጆች ጠፍ​ተ​ዋል።


ሬስ። አቤቱ! ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ አን​ጀ​ቴም ታው​ኮ​ብ​ኛ​ልና ተመ​ል​ከት፤ መራራ ኀዘን አዝ​ኛ​ለ​ሁና ልቤ በው​ስጤ ተገ​ላ​በ​ጠ​ብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመ​ከ​ነ​ችኝ፤ በቤ​ትም ሞት አለ።


ስለ​ዚህ ልባ​ችን ታም​ሞ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ዐይ​ና​ችን ፈዝ​ዞ​አል፤


መካ​ኖች፥ ያል​ወ​ለዱ ማኅ​ፀ​ኖ​ችና ያላ​ጠቡ ጡቶ​ችም የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው የሚ​ሉ​በት ወራት ይመ​ጣ​ልና።


ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ል​ቀስ ኀይል እስ​ኪ​ያጡ ድረስ አለ​ቀሱ።


跟着我们:

广告


广告