Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ጽኑ ቊጣውን በእኛ ላይ ባወረደበት ቀን በእኛ ላይ እንደ ደረሰው ያለ መከራ የደረሰበት ሰው ያለ እንደ ሆነ እናንተ አላፊ አግዳሚዎች እስቲ እዩ ተመልከቱ! ይህ ሁኔታ ለእናንተ ቀላል ነውን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 1:12
18 交叉引用  

በስ​ምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤


ስለ​ዚህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማ​ያት ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ምድ​ርም ከመ​ሠ​ረቷ ትና​ወ​ጣ​ለች።


ስለ ስብ​ራቴ ወዮ​ልኝ! ቍስ​ሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእ​ው​ነት የመ​ከራ ቁስሌ ነው፤ እር​ሱ​ንም መሸ​ከም ይገ​ባ​ኛል አልሁ።


ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።


እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ለመ​ቅ​ሠ​ፍት ወጥ​ቶ​አል፤ የመ​ዓ​ቱ​ንም ጥፋት በኃ​ጥ​ኣን ራስ ላይ አም​ጥ​ቶ​አል፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የል​ቡን አሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ።


ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እር​ሱ​ንም የሚ​መ​ስል የለ​ምና፤ ያ የያ​ዕ​ቆብ መከራ ዘመን ነው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ይድ​ናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ምና ማቅ ልበሱ፤ አል​ቅ​ሱም፤ ዋይም በሉ።


እስ​ራ​ኤል ለአ​ንተ መሳ​ቂያ አል​ሆ​ነ​ምን? ወይስ በሌ​ቦች መካ​ከል ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልን? ስለ እርሱ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ ራስ​ህን ትነ​ቀ​ን​ቃ​ለህ።


ጻዴ። ቃሉን አማ​ር​ሬ​አ​ለ​ሁና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው። እና​ንተ አሕ​ዛብ ሁሉ እባ​ካ​ችሁ ስሙ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም ተመ​ል​ከቱ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከው ሄደ​ዋ​ልና።


አሌፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠ​ቈ​ራት! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ክብር ከሰ​ማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍ​ጣ​ውም ቀን የእ​ግ​ሩን መረ​ገጫ አላ​ሰ​በም።


ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ? ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል? ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው?


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።


跟着我们:

广告


广告