Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 9:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ማን ነው? እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ የሴ​ኬም ልጅ ማን ነው? እርሱ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን? ዜቡ​ልስ የእ​ርሱ ጠባቂ አይ​ደ​ለ​ምን? ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ሰዎች ጋርስ አገ​ል​ጋዩ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ም​ንስ ለዚህ እን​ገ​ዛ​ለን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩባኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቢሜሌክ እንገዛለን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የአቤድ ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፤ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድን ናት? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ረዳት ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፤ ለምን ለአቤሜሌክ እንገዛለን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የዓቤድ ልጅ ጋዓልም እንዲህ አለ፦ “አቤሜሌክ ማን ነው? እኛ የሴኬም ሰዎች ለእርሱ የምንገዛው ለምንድነው? የጌዴዎን ልጅና የእርሱ የጦር መሪ ዜቡር የሐሞርን አባት ሴኬምን ያገለገሉ አይደሉምን? ለምን ለእርሱ እንታዘዛለን? ይልቅስ የጐሣችሁ መሥራች ለሆነው ለሴኬም አባት ለሐሞር ታማኞች ሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የአቤድም ልጅ ገዓል፦ የምንገዛለት አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ምንድር ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልም የእርሱ ሹም አይደለምን? ለሴኬም አባት ለኤሞር ሰዎች ተገዙ፥

参见章节 复制




መሳፍንት 9:28
8 交叉引用  

ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።


የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም።


የሴ​ኬም አባት ኤሞ​ርም ይነ​ግ​ረው ዘንድ ወደ ያዕ​ቆብ መጣ።


በዚ​ያም አንድ ብን​ያ​ማዊ የቢ​ኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚ​ባል የዐ​መፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ከዳ​ዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለ​ንም፦ ከእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድህ ወደ ድን​ኳ​ንህ ተመ​ለስ” ብሎ መለ​ከት ነፋ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ንጉሡ እን​ዳ​ል​ሰ​ማ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለን​ጉሡ፥ “በዳ​ዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእ​ሴ​ይም ልጅ ዘንድ ርስት የለ​ንም። እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራ​ስ​ህን ቤት ተመ​ል​ከት” ብለው መለ​ሱ​ለት። እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ​የ​ቤ​ታ​ቸው ተመ​ለሱ።


የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር መጣ፤ የሰ​ቂማ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተባ​በሩ።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም በአ​ሪማ ተቀ​መጠ፤ ዜቡ​ልም ገዓ​ል​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን በሰ​ቂማ እን​ዳ​ይ​ኖሩ ከለ​ከ​ላ​ቸው።


ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告