Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 8:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጌዴ​ዎን ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ በዓ​ሊ​ምም አም​ላክ ይሆ​ና​ቸው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ጌዴዎን ሞቶ ብዙም ሳይቈይ እስራኤላውያን የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው በዓሊም የተባሉትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤ ለባዓልበሪትም ሰገዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እንዲህም ሆነ፥ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ በኣሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፥ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 8:33
17 交叉引用  

ካህኑ ዮዳሄ ያስ​ተ​ም​ረው በነ​በረ ዘመን ሁሉ ኢዮ​አስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ።


አባ​ቶ​ቻ​ቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው በሚ​ና​ገ​ራት ሕል​ማ​ቸው ሕዝ​ቤን ስሜን ለማ​ስ​ረ​ሳት ያስ​ባሉ።


ዝሙ​ቷም ከንቱ ሆነ፤ እር​ስ​ዋም ከድ​ን​ጋ​ይና ከግ​ንድ ጋር አመ​ነ​ዘ​ረች።


ኢያሱ ባለ​በት ዘመን ሁሉ፥ ከኢ​ያ​ሱም በኋላ በነ​በ​ሩት ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ፥ እስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ለኩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን፥ የሶ​ር​ያ​ንም አማ​ል​ክት፥ የሲ​ዶ​ና​ንም አማ​ል​ክት፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አማ​ል​ክት፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አማ​ል​ክት፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉ፤ አላ​መ​ለ​ኩ​ት​ምም።


ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ቸ​ውን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዉ፤ ሌሎ​ች​ንም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት።


ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም እንጂ፥ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዳ​ይ​ሰሙ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ይሄ​ዱ​ባት የነ​በ​ረ​ች​ውን መን​ገድ ፈጥ​ነው ተዉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም አላ​ደ​ረ​ጉም።


መስ​ፍኑ ግን ከሞተ በኋላ ዳግ​መኛ ተመ​ል​ሰው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ይልቅ እጅግ ይበ​ድሉ፤ ነበር፤ ሂደ​ውም ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው ያመ​ል​ኳ​ቸው ነበር፤ ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም አይ​መ​ለ​ሱም ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።


ጌዴ​ዎ​ንም ምስል አድ​ርጎ ሠራው፤ በከ​ተ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ራታ አኖ​ረው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተከ​ትሎ አመ​ነ​ዘ​ረ​በት፤ ለጌ​ዴ​ዎ​ንና ለቤ​ቱም ወጥ​መድ ሆነ።


የኢ​ዮ​አ​ስም ልጅ ጌዴ​ዎን በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ሞተ፤ በአ​ብ​ያ​ዜ​ራ​ው​ያ​ንም ከተማ በኤ​ፍ​ራታ በነ​በ​ረ​ችው በአ​ባቱ በኢ​ዮ​አስ መቃ​ብር ተቀ​በረ።


ወደ እር​ሻ​ውም ወጡ፤ ወይ​ና​ቸ​ው​ንም ለቀሙ፤ ጠመ​ቁ​ትም፤ የደ​ስ​ታም በዓል አደ​ረጉ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ረገ​ሙት።


ከበ​ዓ​ልም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፤ በዚ​ያም አቤ​ሜ​ሌክ ወን​በ​ዴ​ዎ​ች​ንና አስ​ደ​ን​ጋ​ጮ​ችን ቀጠ​ረ​በት፤ እነ​ር​ሱም ተከ​ት​ለ​ውት ሄዱ።


በሰ​ቂ​ማም ግንብ ውስጥ የነ​በሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ በዓል ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ።


跟着我们:

广告


广告