Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 8:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ስለ ነበሩ የወ​ርቅ ጕትቻ ነበ​ራ​ቸ​ውና ጌዴ​ዎን፥ “ሁላ​ች​ሁም ከም​ር​ኮ​አ​ችሁ ጕት​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ት​ሰ​ጡኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱም፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጕትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጉትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጉትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እስማኤላውያን የጆሮ ጉትቻ ማድረግ ልማዳቸው ስለ ነበረ የጌዴዎን ወታደሮች ጉትቻዎቻቸውን ማርከው ነበር፤ ጌዴዎንም “እያንዳንዳችሁ የማረካችሁትን ጉትቻ ስጡኝ” ብሎ ለመናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እስማኤላውያንም ስለ ነበሩ የወርቅ ጉትቻ ነበራቸውና ጌዴዎን፦ ሁላችሁ ከምርኮአችሁ ጉትቻችሁን እንድትሰጡኝ እለምናችኋለሁ አላቸው።

参见章节 复制




መሳፍንት 8:24
17 交叉引用  

ግመ​ሎ​ቹም ከጠጡ በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው​ዬው አንድ አንድ ወቄት የሚ​መ​ዝን የወ​ርቅ ጉትቻ፥ ለእ​ጆ​ች​ዋም ዐሥር ወቄት የሚ​መ​ዝን ጥንድ የወ​ርቅ አም​ባር አወጣ፤


ሎሌ​ውም የብ​ርና የወ​ርቅ ጌጥ፥ ልብ​ስም አወጣ፤ ለር​ብ​ቃም ሰጣት፤ ዳግ​መ​ኛም ለአ​ባ​ቷና ለእ​ናቷ እጅ መንሻ ሰጣ​ቸው።


የሣራ ባሪያ ግብ​ፃ​ዊቱ አጋር ለአ​ብ​ር​ሃም የወ​ለ​ደ​ች​ለት የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የይ​ስ​ማ​ኤል ትው​ልድ ይህ ነው፤


የይ​ስ​ማ​ኤ​ልም የል​ጆቹ ስም በየ​ስ​ማ​ቸ​ውና በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እን​ዲህ ነው።


በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።


እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።


እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።


በከ​ተ​ማ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት የከ​ተ​ማው ሰዎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ችም ኤል​ዛ​ቤል እን​ዳ​ዘ​ዘ​ቻ​ቸ​ውና ወደ እነ​ርሱ በተ​ላ​ከው ደብ​ዳቤ እንደ ተጻ​ፈው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረጉ። ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም የብ​ር​ንና የወ​ር​ቅን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንም ተዋሱ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ በጆ​ሮ​ዎ​ቻ​ቸው ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች ወደ አሮን አመ​ጡ​ለት።


ከእ​ጃ​ቸ​ውም ተቀ​ብሎ በመ​ቅ​ረጫ ቀረ​ጸው፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ጥጃም አደ​ረ​ገው፤ እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው” አላ​ቸው።


ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈጥ​ነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተ​ሠራ የጥጃ ምስል ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም፤ ሠዉ​ለ​ትም፤


የክ​ብ​ሩ​ንም ጌጥ ወደ ትዕ​ቢት ለወጡ፤ የር​ኵ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ምስ​ሎች አደ​ረ​ጉ​ባት፤ ስለ​ዚህ እኔ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ርኩስ አድ​ር​ጌ​አ​ታ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “መስ​ጠ​ትን ፈቅ​ደን እን​ሰ​ጥ​ሃ​ለን” ብለው መለ​ሱ​ለት። መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም አነ​ጠፉ፤ ሰውም ሁሉ የም​ር​ኮ​ውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ።


እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና የወ​ይን ጠጄን፥ ለሸ​ላ​ቾ​ቼም ያረ​ድ​ሁ​ትን ሥጋ ወስጄ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ለማ​ላ​ው​ቃ​ቸው ሰዎች እሰ​ጣ​ለ​ሁን?”


跟着我们:

广告


广告