Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ‘ማንም የፈራ ቢኖር የገለዓድን ተራራ ትቶ ወደ መጣበት ይመለስ’ ብለህ ለሕዝቡ ዐውጅ።” ስለዚህ ሃያ ሁለቱ ሺሕ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺሕ ብቻ ቀሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ ዐሥርም ሺህ ቀሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ ለሕዝቡ ‘ከመካከላችሁ ፈሪና ድንጉጥ የሆነ ሰው ካለ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ እኛም በዚህ በገለዓድ ተራራ ላይ እንቈያለን’ ብለህ ንገራቸው።” በዚህ ምክንያት ኻያ ሁለቱ ሺህ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺህ ቀሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ አሥርም ሺህ ቀሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 7:3
7 交叉引用  

ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፤ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።


እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።’ ”


ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


ወደ ምና​ሴም ነገድ ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ሱም ከኋ​ላው ሆኖ ጮኸ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ አሴ​ርና ወደ ዛብ​ሎን ወደ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊቀ​በ​ሉ​አ​ቸው ወጡ።


跟着我们:

广告


广告