Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ ወደ ጋዛም እስ​ከ​ሚ​ደ​ርሱ የእ​ር​ሻ​ቸ​ውን ፍሬ ያጠፉ ነበር፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ምንም አይ​ተ​ዉም ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ዎ​ችም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይ​ተ​ዉም ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱም በምድሪቱ ላይ ሰፍረው እስከ ጋዛ ያለውን ሰብል በማጥፋት አንዳችም የእህል ዘር ለእስራኤል አያስተርፉም፣ የበግም ሆነ የከብት ወይም የአህያ መንጋ አይተዉም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነርሱም በምድሪቱ ላይ ሰፍረው እስከ ጋዛ ያለውን ሰብል በማጥፋት አንዳችም የእህልዘር አያስተርፉም፥ የበግም ሆነ የከብት ወይም የአህያ መንጋ አይተዉም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በአገሪቱ ላይ በመስፈር በጋዛ ዙሪያ እስካለው ስፍራ ድረስ የምድሪቱን ሰብል ያጠፉ ነበር፤ የበግ፥ የከብትና የአህያ መንጋቸውንም እየነዱ ስለሚወስዱባቸው ለእስራኤላውያን ምንም ነገር አያስቀሩላቸውም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእነርሱም ላይ ይሰፍሩ ነበር፥ እስከ ጋዛም ድረስ የምድሩን ቡቃያ ያጠፉ ነበር፥ ምግብንም ለእስራኤል አይተዉም ነበር፥ በግ ወይም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይተዉም።

参见章节 复制




መሳፍንት 6:4
12 交叉引用  

የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ወሰን ከሲ​ዶን እስከ ጌራ​ራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳ​ማና ወደ ሴባ​ዮም እስከ ላሳ ይደ​ር​ሳል።


ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።


መከ​ር​ህ​ንና እን​ጀ​ራ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ይበ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በጎ​ች​ህ​ንና ላሞ​ች​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ ወይ​ን​ህ​ንና በለ​ስ​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ የም​ት​ታ​መ​ና​ቸ​ውን የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ያጠ​ፋሉ።”


እኔም እን​ዲህ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ሀ​ትን፥ ክሳ​ት​ንም፥ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ዝዝ፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠፋ ትኩ​ሳት አወ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም በከ​ንቱ ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችሁ ይበ​ሉ​ታ​ልና።


“ሌቦች ቢመ​ጡ​ብህ፥ ወይም ወን​በ​ዴ​ዎች በሌ​ሊት ቢመጡ፥ የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ርቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወይ​ንም የሚ​ቈ​ርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃር​ሚያ አያ​ስ​ቀ​ሩ​ምን?


ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ፥ ድካ​ም​ህ​ንም ሁሉ የማ​ታ​ው​ቀው ሕዝብ ይበ​ላ​ዋል፤ አን​ተም ሁል​ጊዜ የተ​ጨ​ነ​ቅህ፥ የተ​ገ​ፋ​ህም ትሆ​ና​ለህ።


እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ የከ​ብ​ት​ህን ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ይበ​ላል፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ አይ​ተ​ው​ል​ህም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤


跟着我们:

广告


广告