መሳፍንት 6:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን አለው፥ “በቍጣህ አትቈጣኝ፤ ደግሞ አንዲት ነገር ልናገር፤ ጠጕሩ ብቻውን ደረቅ ይሁን፤ በምድሩም ላይ ጠል ይውረድ።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም39 ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደ ገና ልጠይቅ። በጠጕሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደገና ልጠይቅ። በጠጉሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 ቀጥሎም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ እንደገና አንድ ጊዜ እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ይኸውም በበግ ጠጒሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ምልክት እንዲታይ ልጠይቅ፤ በዚህን ጊዜ የጠጒሩ ባዘቶ ደረቅ ሆኖ በዙሪያው ያለው ምድር እርጥብ እንዲሆን አድርግልኝ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፦ እኔ ይህን አንድ ጊዜ ስናገር አትቈጣኝ፥ እኔ ይህን አንድ ጊዜ በጠጉሩ፥ እባክህ፥ ልፈትን፥ አሁንም በጠጉሩ ብቻ ላይ ደረቅ ይሁን፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ጠል ይሁን አለው። 参见章节 |