Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሔ​ቤ​ርም ሚስት ኢያ​ዔል የድ​ን​ኳ​ኑን ካስማ ወሰ​ደች፤ በሁ​ለ​ተኛ እጅ​ዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረ​በች፤ በጆሮ ግን​ዱም ካስ​ማ​ውን ቸነ​ከ​ረ​ች​በት፤ እር​ሱም ደክሞ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበ​ርና ካስ​ማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እር​ሱም ከእ​ግ​ርዋ በታች ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ተዘ​ር​ሮም ሞተ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሔቤር ሚስት ኢያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፣ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፣ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋራ ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሲሣራ በጣም ደክሞት ስለ ነበር ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ ከዚህ በኋላ የሔቤር ሚስት ያዔል መዶሻና የድንኳን ካስማ ወስዳ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ካስማውንም በጆሮ ግንዱ ጠልቆ መሬት እስኪነካ ድረስ ቸነከረችው፤ እርሱም ሞተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሔቤርም ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች፥ በእጅዋም መዶሻ ያዘች፥ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረበች፥ በጆሮግንዱ ካስማውን ቸነከረች፥ እርሱም ደክሞ እንቀላፍቶ ነበርና ካስማው ወደ መሬት ጠለቀ፥ እርሱም ሞተ።

参见章节 复制




መሳፍንት 4:21
12 交叉引用  

ተነሥ፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አንተ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝን ሁሉ መት​ተ​ሃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ጥርስ ሰብ​ረ​ሃ​ልና።


መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የመ​ካ​ሪ​ዎ​ች​ንም ምክር እን​ቃ​ለሁ።”


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​በ​ኞ​ችን ሊያ​ሳ​ፍር የዚ​ህን ዓለም ሰነ​ፎች መረጠ፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ደካ​ሞች መረጠ።


የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።


ናዖ​ድም በተ​ነሣ ጊዜ ግራ እጁን ዘር​ግቶ ከቀኝ ጎኑ ሰይ​ፉን መዘዘ፤ ዔግ​ሎ​ም​ንም ሆዱን ወጋው፤


ከእ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ናት ልጅ ሴሜ​ጋር ተነሣ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስድ​ስት መቶ ሰው በበሬ መው​ጊያ ገደለ፤ እር​ሱም ደግሞ እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ።


እር​ሱም፥ “ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠ​ይ​ቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪ​ዋ​ለሽ” አላት።


እነ​ሆም፥ ባርቅ ሲሣ​ራን ሲያ​ባ​ርር ኢያ​ዔል ልት​ገ​ና​ኘው ወጥታ፥ “ና፤ የም​ት​ሻ​ውን ሰው አሳ​ይ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ እነ​ሆም፥ ሲሣ​ራን ወድቆ፥ ሞቶም አገ​ኘው፤ ካስ​ማ​ውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ።


ዲቦ​ራም፥ “በእ​ው​ነት ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በሴት እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና በዚህ በም​ት​ሄ​ድ​በት መን​ገድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ንም” አለ​ችው። ዲቦ​ራም ተነ​ሥታ ከባ​ርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው።


跟着我们:

广告


广告