መሳፍንት 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመቀበል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አትፍራም” አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ በምንጣፍም ሸፈነችው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ኢያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበለችውና፣ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበ ለችውና፥ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ያዔልም ሲሣራን ልትቀበለው ወጥታ “ጌታዬ ና፥ ወደ ድንኳኔ ግባ፤ ከቶ አትፍራ” አለችው፤ እርሱም ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ በልብስ ሸፈነችው፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጥታ፦ ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፥ አትፍራ አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፥ በመጎናጸፊያዋም ሸፈነችው። 参见章节 |