Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ናዖ​ድም ወደ እርሱ ገባ፤ እር​ሱም በበጋ ቤቱ ሰገ​ነት ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ ነበር። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክት ለአ​ንተ አለኝ” አለው። ዔግ​ሎ​ምም ከዙ​ፋኑ ተነሣ፥ ቀረ​በ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ናዖድ ቀረብ ብሎ፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በዚያን ጊዜ ንጉሡ በጣራው ላይ ባለው ነፋሻ ክፍል ለብቻው ተቀምጦ ሳለ፥ ኤሁድ ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “ከእግዚአብሔር ለአንተ የተላከ መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ብድግ ብሎ ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ናዖድም ወደ እርሱ ቀረበ፥ እርሱም በሰገነት ቤት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፦ የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ አለ። ከዙፋኑም ተነሣ።

参见章节 复制




መሳፍንት 3:20
11 交叉引用  

“ሂድና ለዳ​ዊት እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሦስት ነገ​ሮ​ችን በፊ​ትህ አኖ​ራ​ለሁ፤ አደ​ር​ግ​ብህ ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ምረጥ።”


ዕዝ​ራም የሕ​ዝቡ ሁሉ የበ​ላይ ነበ​ረና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት መጽ​ሐ​ፉን ገለጠ፤ በገ​ለ​ጠ​ውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ።


አቤቱ፥ ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና፥ የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አላ​ደ​ረ​ግ​ኸ​ኝ​ምና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?


ንጉ​ሡም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ወር በክ​ረ​ምት በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ቤት ተቀ​ምጦ ነበር፤ በፊ​ቱም እሳት ይነ​ድድ ነበር።


የክ​ረ​ም​ቱ​ንና የበ​ጋ​ዉን ቤት እመ​ታ​ለሁ፤ በዝ​ሆ​ንም ጥርስ የተ​ለ​በ​ጡት ቤቶች ይጠ​ፋሉ፤ ሌሎ​ችም ታላ​ላ​ቆች ቤቶች ይፈ​ር​ሳሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።


በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፤ ስማ፤ የሶ​ፎር ልጅ ሆይ፥ ምስ​ክር ሁነህ አድ​ምጥ፤


ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ።


ናዖ​ድም በተ​ነሣ ጊዜ ግራ እጁን ዘር​ግቶ ከቀኝ ጎኑ ሰይ​ፉን መዘዘ፤ ዔግ​ሎ​ም​ንም ሆዱን ወጋው፤


跟着我们:

广告


广告