መሳፍንት 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እነርሱም፥ “እነሆ፥ በቤቴል በመስዕ በኩል፥ ከቤቴልም ወደ ሰቂማ በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል በሌብና በዐዜብ በኩል ባለችው በሴሎ የእግዚአብሔር በዓል በየዓመቱ አለ” አሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ይሁን እንጂ ከቤቴል በስተ ሰሜንና ከቤቴል ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በስተምሥራቅ እንዲሁም ከለቦና በስተ ደቡብ ባለችው በሴሎ የእግዚአብሔር በዓል በየዓመቱ ይከበራል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ይሁን እንጂ ከቤቴል በስተ ሰሜንና ከቤቴል ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በስተ ምሥራቅ እንዲሁም ከለቦና በስተ ደቡብ ባለችው በሴሎ የጌታ በዓል በየዓመቱ ይከበራል።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ከዚህ በኋላ “በየዓመቱ በሴሎ ለእግዚአብሔር የሚዘጋጀው በዓል እነሆ ቀርቦአል” በማለትም አሰቡ፤ ሴሎ ከቤትኤል በስተ ሰሜን፥ ከለቦና በስተ ደቡብ፥ በቤትኤልና በሴኬም መካከል ካለው መንገድ በስተ ምሥራቅ ነበረች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እርሱም፦ እነሆ፥ በቤቴል በሰሜን በኩል፥ ከቤቴልም ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል፥ በለቦና በደቡብ በኩል ባለችው በሴሎ የእግዚአብሔር በዓል በየዓመቱ አለ አሉ። 参见章节 |